በኦሮምያ ክልል ምሥራቅ ወለጋ ዞን ነቀምቴና በምዕራብ ወለጋ ጊምቢ ከተሞች ከትናንት ምሽት አንስቶ ዛሬም የተካሄዱ ሕዝባዊ ተቃውሞዎች በሰላም መጠናቀቃቸው ታውቋል።
በኦሮምያ ክልል ቦረና ዞን ውስጥ በምትገኘው ሜጋ ከተማ አቅራቢያ በነዋሪዎችና በመከላከያ ኃይሎች መካከል በተፈጠረ ግጭት አራት ሰዎች መገደላቸውና 18 መቁሰላቸው ተገለፀ።
የአሜሪካ ኤምባሲ ዜጎቹ ወደ ሻሸመኔ ከመጓዝ እንዲቆጠቡ መከረ።
ላይቤሪያዊያን መጭ ፕሬዚዳንታቸውንና እንደራሴዎቻቸውን ለመምረጥ ይወጣሉ። አሁን ያሉት ፕሬዚዳንት ኤን ጆንሰን ሰርሊፍ ለሁለት የሥልጣን ዘመናት ካገለገሉ በኋላ በያዝነው የአውሮፓ ዓመት መጨረሻ ይሰናበታሉ። ፉክክሮቹ ሁሉ እያተኮሩ ያሉት ሃገሪቱን በእጅጉ ባደቀቃት ኢቦላ ወረርሽኝ ምክንያት በተጎዱት መሠረተ ልማትና የጤና ጥበቃ አገልግሎት ላይ ነው።
መስከረም 23/1928 ዓ.ም (ዛሬ፤ ልክ የዛሬ 82 ዓመት) ፋሽስት ጣልያን ኢትዮጵያን ያኔ አቢሲኒያን ወረረች። ከሰባት ወራት ውጊያ በኋላ የጠላት ጦር አዲስ አበባን ያዘና የዱር የገደል ፍልሚያው ለመጭዎች አራት ዓመታት ተኩል ያህል ቀጠለ። በዚህ የያኔው የመንግሥታት ኅብረት (ሊግ አፍ ኔሽንስ) አባላት በነበሩ ሁለት ሀገሮች መካከል በተካሄደ ውጊያ ከኢትዮጵያ ከ275 ሺህ በላይ ተዋጊዎች ተገደዋል፤ ለግማሽ ሚሊዮን በላይ ጦረኞች ቆስለዋል፡፡
በኦሮምያና በሶማሌ እንዲሁም በደቡብና በኦሮምያ አዋሣኝ አካባቢዎች ላይ እየታዩ ያሉት ግጭቶች ለሃገሪቱ አጠቃላይ የወደፊት ዕጣ አስጊ ናቸው ሲል የኢትዮጵያ ሶሻል ዴሞክራቲክ ፓርቲ አስጠንቅቋል።
በጦርነትና ብጥብጥ ለተዋጠችው ማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ ወደ ሰላም መሄጃው መንገድ አጥፍቶ አለመቀጣትን መዋጋት መሆኑን የማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት አስታወቁ።
ኢትዮጵያ በያዝነው የአውሮፓ ዓመት በዓለም እጅግ ፈጣኗ ምጣኔ ኃብት ትሆናለች ተብሎ ተተንብይዋል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሣለኝ አስታውቀዋል።
የሲሊከን ቫሊ ታሪክና ወጣ ገባውን ለማየት፣ በዛው ያሉ አፍሪካውያን ቴክኖሎጂስቶችንና የሥራ ፈጣሪዎችን ለማግኘት እና ለማነጋገር ወደ ካሊፎርኒያ ሳንፍራንሲስኮ የተጓዘው ሰሎሞን አባተ በተለያዩ የሞያ ዘርፎች የተሰማሩ ኢትዮጵያውያንን አግኝቶ አነጋገሯል፡፡ ለዛሬ ከፕሮፌሰር አዱኛው ወርቁ ጋር በሙዚቃ፣ በቤተሠብ፣ በሥራ፣ በሀገር ጉዳይ የመሳሰሉት ጉዳዬችን አንሰተው ተጨዋውተዋል፡፡
አፋጣኝ ዕርምጃ ካልተወሰደ በመጪዎቹ ሦስት ወራት ውስጥ 6መቶ ሺህ ሕጻናት በረሃብና በበሽታ እንደሚረግፉ /ሴቭ ዘ ችልድረን/ አስጠነቀቀ።
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የፀጥታ ጥበቃ ምክር ቤት በአጀንዳ፣ የሠላም ማስከበር ተልዕኮዎቹን ሰለማሻሻል መከረ፡፡
እንደ ዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ሃገራቸውን ከማንም በፊት እንደሚያስቀድሙ ሚስተር ዶናልድ ትረምፕ በድጋሚ አረጋገጡ።
ቪዥን ኢትዮጵያ ያዘጋጀው "የዴሞክራሲያዊ ተቋማት ግንባታ በኢትዮጵያ" ተብሎ የተሰየመ የውይይት ጉባዔ የፊታችን ቅዳሜና ዕሁድ ዋሺንግተን ዲሲ ውስጥ ይካሄዳል።
በኦሮምያና በሶማሌ ክልሎች መካከል እየታየ ያለው ግጭትና ጥቃት የብዙ ኢትዮጵያዊያንን ሕይወት በልቷል።
በኦሮሚያና በሶማሌ ክልሎች አዋሳኝ ወረዳዎች ላይ ተስፋፍተው እጅግ የበዛ ሕይወት ያጠፉት ጥቃቶችና ግጭቶትን ለማስቆም ጥረት እየተደረገ ባለበት ጊዜ ባሌ ዞን ውስጥም ትናንት በተፈፀመ ጥቃት 16 ሰው መገደሉ ተገለፀ፡፡
በኦሮምያና በሶማሌ ክልሎች ወሰኖች ባሉ ወረዳዎች ውስጥ እየተካሄደ ካለው የጥቃት እርምጃዎችና ግጭቶች ጋር በተያያዙ ምክንያቶች ከተፈጠረው የፀጥታ ቀውስ ጋር ተያይዞ ከሰማሌ ክልል የተፈናቀሉ ከአርባ ሺህ እስከ ሃምሣ ሺህ የሚሆኑ የኦሮሞ ተፈናቃዮች ምሥራቅ ሃረርጌ መግባታቸውን የዞኑ አስተዳዳሪ ማምሻውን ለቪኦኤ ገልፀዋል።
ከመስከረም 2/2010 ዓ.ም አንስቶ በተፈጠሩ ግጭቶች በአወዳይ በጅጅጋና እና በጭናቅሰን ከተሞች እና አካባቢዎቻቸው የሁከት የጅምላ ግድያ አና የጅምላ መፈናቀል ሁኔታዎች ታይተዋል፡፡
በሶማሌ ክልልና በኦሮሚያ አጎራባች አካባቢዎች ላይ ከተፈፀመው ጥቃቶችና እየታዩ ካሉ ግጭቶች ጋር በተያያዙ ሁከት አዘል ጥቃቶች አወዳይ ከተማ ውስጥ ቁጥሩ የበዛ ሰው ሕይወት መጥፋቱ ተገልጿል፡፡
መስከረም አንድ በአሜሪካዊያን ዘንድ በከበደ ኀዘን ታስቦ የሚውል ቀን ነው። ልክ የዛሬ 16 ዓመት መስከረም 1994 ዓ.ም. በበረራ ቁጥር 77 የተመዘገበ የአሜሪካን ኤይርላይንስ አይሮፕላን ተሣፍረውበት ከነበሩ 59 መንገደኞች ጋር ተጠልፎ የዩናይትድ ስቴትስ የመከለከያ ሚኒስቴርን መታ። ያኔ ፔንታገን ውስጥ የነበሩ 125 ሰዎች ተገደሉ።
ኧርማ ተብሎ የተሰየመው ዝናብ የቀላቀለ እጅግ ኃይለኛ የውቅያኖስ ማዕበል ዛሬ፤ ሰኞ ረገብ ብሎ ሰሜን ፍሎሪዳና ደቡባዊ ጆርጅያን እያዳረሰ ነው።
ተጨማሪ ይጫኑ