ዩናይትድ ስቴትስ ኤችአይቪን ለመቆጣጠር ባደረገችው ጥረት ግዙፍ ውጤት ማስመዝገቧ ተገልጿል።
በሃገር ውስጥና በውጭ ያሉትን ሁለቱን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋኅዶ ቤተክርስትያን ሲኖዶሶች ወደ አንድ ለማምጣት አዲስ ጥረት ተጀምሮ እየተካሄደ ነው።
ከ1985 እስከ 1987 ዓ.ም. በዩኒቨርሲቲ ኦቭ ዚምባብዌ፣ ከዚያም በደቡብ አፍሪካው ዩኒቨርሲቲ ኦቭ ዊትዋተርስትራድ እና በዩናይትድ ስቴትስ ዴንቨር-ኮሎራዶ ሜትሮፖሊታን ስቴት ዩኒቨርሲቲ የፋይናንስና የሂሣብ አያያዝ ፕሮፌሰር ሆነው አገልግለዋል፤ አሁንም እየሠሩ ያሉት ፕሮፌሰር ሚንጋ ነጋሽ ዚምባብዌ ባለፉ አርባ ዓመታት ያለፈችበትን ጉዞ ጠቅለል አድርገው ለቪኦኤ አጫውተዋል።
የሮበርት ሙጋቤ የ37 ዓመታት አስተዳደር ዘመን ሲያከትም ዚምባብዌ ዛሬ አዲስ ፕሬዚዳንት አግኝታለች።
ለሮበርት ሙጋቤ ውድቀት አንዱ ምክንያት እጅግ ለተራዘመ ጊዜ ሥልጣን የሙጥኝ ብለው መቆየታቸው መሆኑንና ቀደም ብለው አስረክበው ቢሆን ኖሮ እንደጀግና እንደተወደሱ ይኖሩ እንደነበር ሻለቃ ዳዊት ወልደጊዮርጊስ ለቪኦኤ በሰጡት ትንታኔ አብራርተዋል።
በኦሮምያ ክልል ምሥራቅ ጉጂ ዞን ሰባ ቦሩ ወረዳ የቀንጥቻ ቀበሌ ነዋሪዎች ዛሬ ብዙ ሰው የተሣተፈበት ሰላማዊ ሰልፍ አድርገዋል። ጥያቄዎቻቸው ከአካባቢ ጥበቃ፣ የልማት ተጠቃሚነትና የሥራ ዕድል ጋር የተያያዙ መሆናቸውን ነዋሪዎችና የወረዳው አስተዳዳሪ ለቪኦኤ ገልፀዋል።
ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ኢንዲያና ግዛት ላፋዬት ከተማ የሚገኘው ፐርዱ ዩኒቨርሲቲ የግብርና ተመራማሪ የሆኑት ዶ/ር ገቢሳ ኢጀታ በማሽላ ዘረመል ላይ ለሚያካሂዱት ጥናት የአምስት ሚሊየን ዶላር ስጦታ አገኙ።
የጀርመኗ ከተማ ቦን ላይ ለሁለት ሣምንታት እየተካሄደ ያለው የአየር ንብረት ጉባዔ ነገ፤ ዓርብ ይጠናቀቃል።
የዚምባብዌው የረዥም ጊዜ መሪ ሮበርት ሙጋቤ ዋና ከተማዪቱ ሃራሬ ውስጥ “በቁም እሥር” ላይ መሆናቸውን የደቡብ አፍሪካው ፕሬዚዳንት ጄከብ ዙማ አረጋግጠዋል። ሮበርት ሙጋቤ ከ37 ዓመታት የፕሬዚዳንትነት ዘመን በኋላ ወታደራዊ ድጋፍ ባለው እንቅስቃሴ ዛሬ ከመንበረ ሥልጣናቸው ተገፍተው ወጥተዋል።
የእሥያን የንግድ አቅጣጫ አስመልክቶ የዩናይትድ ስቴትስና የቻይና ፕሬዚዳንቶች ለአካባቢው የንግድ መሪዎች ባደረጓቸው ንግግሮች ውስጥ ጨርሶ የሚጣረሱ አመለካከቶችን አንፀባርቀዋል።
የሩቅ ምሥራቅ እስያን አካባቢ ነፍሰ ገዳይ ካሉት የሰሜን ኮሪያ አገዛዝ ዩናይትድ ስቴትስና ቻይና ተባብረው ነፃ እንዲያወጡ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ቤጂንግ ላይ ጥሪ አስተላልፈዋል።
አሚሶም በሚል ምኅፃር የሚጠራው የአፍሪካ ሕብረትና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሰላም አስከባሪ ኃይል ከሶማሊያ መውጣት እንደሚጀምር እዚያው የሚገኙት የተልዕኮው አዛዥ አስታወቁ።
ኢትዮጵያ ውስጥ በ1960ዎቹ መጨረሻ ላይ በተካሄደው ቀይ ሽብር ውስጥ እጃቸው አለ የተባሉ ኢትዮጵያዊ ሆላንድ ውስጥ ተይዘው አንድ የሄግ ፍርድ ቤት ቀረቡ።
ኢትዮጵያ ውስጥ እሥረኞች የሚያዙበት ሁኔታ የጭካኔ አያያዝ የተደባለቀበት እንደሆነ የሚገልፁ ክሦች ይሰማሉ፤ የወኅኒ ቤቶች አስተዳደር ግን ያስተባብላል።
ሰማያዊ ፓርቲ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ከተጣለበት ጊዜ አንስቶ ላለፈው አንድ ዓመት የሚሆን ጊዜ የመጀመሪያዊን ሕዝባዊ ስብሰባ ትናንት አዲስ አበባ ላይ አካሂዷል።
በኢትዮጵያ እሥር ቤቶችና ፖሊስ ጣቢያዎች ውስጥ የሕይወት መጥፋትን የጨመሩ ኢሰብአዊ አያያዞች ይፈፀማሉ የሚሉ ተከታታይና ተደራራቢ እሮሮዎች እየተሰሙ ናቸው።
ኢትዮጵያ ላለፉት አራት ዓመታት ከልጅነት ልምሻ ነፃ መሆኗን አስታውቃለች።
የኢትዮጵያ አየር ኃይል የመጀመሪያ ካዴቶችና አብራሪዎች አንዱ የነበሩት ኮሎኔል ጋዲሳ ጉማ በዘጠና ሰባት ዓመት ዕድሜአቸው ዛሬ አረፉ።
ላለፉት ተከታታይ ሣምንታት በየሥፍራው ሰልፎች ሲካሂዱባት በሰነበተችው ኦሮምያ ዛሬም በመቱ፣ በጊምቢና በፍቼ “ብዙ ሰው ተገኝቶባዋል” የተባሉ ሰላማዊ ሰልፎች መካሄዳቸው ተገልጿል።
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ ከኢራን ጋር የተገባውን የኒኩሌር መርኃግብር ውል እንደማያድሱ አስታወቁ።
ተጨማሪ ይጫኑ