የኢየሱስ ክርስቶስ ልደት ነው ብለው በዓለም ዙሪያ ብዙ ክርስትያን ምዕመናን የሚያምኑበት የዛሬው የገና በዓል በፍልስጥዔማዊያን ይዞታ ሥር ባለችው ቤተልሄም እየተከበረ ይገኛል።
ዛሬ የፈረንጅ ገና ነው /በኢትዮጵያዊያን አጠራር/ ወይም ባለቤቶቹ እንደሚሉት ክሪስማስ።
የቀድሞ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትርና አምባሣደርም ሆነው ያገለገሉት ኸርማን ኮኸን ባለፈው ሣምንት ውስጥ በትዊተር ባወጡት ሃሣብ ለሕዝባዊ ወያነ ሐርነት ትግራይ - ሕወሐት መሪዎች ምክር አዘል መልዕክት አስተላልፈዋል።
የዩጋንዳ እንደራሴዎችና የፓርላማው ፖሊስ ትናንት ግብ ግብ ገጥመዋል። ምክንያቱ እንደራሴዎቹ የሃገሪቱን ፕሬዚዳንት የዕድሜ ጣሪያ ገደብ ጉዳይ አንስተው እየተወያዩ ሣሉ ወታደሮች በፓርላማው ግቢ ውስጥ ታዩ መባሉ ነበር። “በዚያው የቃላቱ መሠናዘር ተቋርጦ የአካል ትንቅንቁ ተጀመረ” ብላለች የካምፓላ ሪፖርተራችን ሃሊማ አቱማኒ።
ምሥራቅ ሃረርጌ ጨለንቆ ውስጥ በ15 ሰዎች ላይ የተፈፀመው ግድያ “የመብት ጥያቄ በማንሳታቸው ብቻ የተፈፀመባቸው ዘግናኝ እርምጃ ነው” ሲሉ የዞኑ የመንግሥት ኮምዩኒኬሽንስ ጉዳዮች ፅሕፈት ቤት ምክትል ኃላፊ አማርረዋል።
በወለጋ ዩኒቨርሲቲ የሻምቡ ግቢ ውስጥ ትናንት በተማሪዎች መካከል በተነሣ ግጭትና ሁከት ሁለት የትግራይ ተማሪዎች መገደላቸው ተገልጿል።
ዩናይትድ ስቴትስ ካሉባት የበረቱ ፈተናዎች አንዱ በወል መጠሪያ ‘ኦፒዮይድስ’ የሚባሉ አደንዛዥና ሕመም አስታጋሽ መድኃኒቶች ሥር የሰደደ ቀውስ ነው።
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ለኢየሩሣሌም የእሥራኤል ዋና ከተማ በይፋ እውቅና በመስጠታቸው ከአረቢ ዓለም እንዲሁም ከአውሮፓና ከሌሎችም አካባቢዎች ነቀፋዎችን አስከትሎባቸዋል።
ፍልስጥዔማዊያኑ “የቁጣ ቀናት” ብለው በጠሯቸው ሦስት ተከታታይ ቀናት ተቃውሟቸውን ለማሰማት ጥሪዎችን እያስተላለፉ ናቸው።
የመን ዋና ከተማ ሰንዓ ውስጥ ባለፉት አራት ቀናት በተካሄዱ ከባድ ውጊያዎች ከ230 በለይ ሰው መገደሉንና ቁጥራቸው ከአራት መቶ በላይ የሆኑ ሌሎች ሰዎች መጎዳታቸውን በየመን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ ጉዳዮች ከፍተኛ አስተባባሪ ለቪኦኤ ገለፁ።
የመን ዋና ከተማ ሳንዓ ውስጥና በአካባቢዋ የቀድሞ አጋሮች በነበሩት የሁጢ አማፂያንና በቀድሞው ፕሬዚዳንት አሊ አብደላ ሳለህ ታማኝ ኃይሎች መካከል በተቀሰቀሰውና ላለፉት በርካታ ቀናት እየተካሄደ ባለው የከበደ ውጊያ በአሥሮች የሚቆጠሩ ሰዎች መገደላቸው እየተሰማ ነው።
የቀድሞ የየመን ፕሬዚደንት አሊ አብዱላ ሳልህ መገደላቸውን ፓርቲአቸው አረጋገጠ። በማህበራዊ መገናኛዎች ላይ ‘የርሳቸው አስከሬን ነው’ የተባለ ምሥል የያዘ ቪዲዮ እየታየ ነው።
ኢትዮጵያ ውስጥ ኤችአይቪ በደሙ ውስጥ የሚገኘው ሰው ቁጥር ከ718 ሺህ በላይ መሆኑንና ከእነዚህም መካከል ሕክምና እየተከታተሉ ያሉት 69 ከመቶ የሚሆኑት መሆናቸውን የኢትዮጵያ ኤችአይቪ/ኤድስ መከላከያና መቆጣጠሪያ ፅሕፈት ቤት አስታወቀ።
ጋዜጠኛ፣ ደራሲ፣ ፀሐፌ-ተውኔት፣ ገጣሚ፣ ድምፃዊ፣ ተዋናይ፣ ዲያቆንና የሌሎችም በርካታ ክህሎቶች፣ አስተዋፅዖ፣ ክብርና ሽልማቶች ባለቤቱ ሣሙዔል ፈረንጅ አረፈ።
እንግሊዝ ውስጥ ያለ እጅግ ፅንፈኛ ነው የሚባል አንድ ቡድን አባል ኢንተርኔት ላይ ያወጣቸውን ቪድዮዎች የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ መልሰው ትዊት በማድረጋቸው የእንግሊዝ እንደራሴዎች የበረታ ቁጣ እያሰሙ ናቸው።
ሊብያ ውስጥና በሌሎችም የዓለም ክፍሎች መውጫ አጥተው የሚገኙ ዜጎቻቸውን ለመመለስ የናይጀሪያው ፕሬዚዳንት ሙሐማዱ ቡሃሪ ቃል ገቡ።
ሩሲያ በጎረቤቶቿ ላይ በተለይ በምርጫ ሂደቶቻቸው ውስጥ ጣልቃ እየገባች ምስቅልቅል ለመፍጠርና ኢ-ዴሞክራሲያዊ አስተሳሰቦችን ለመጫን በተከታታይ ትከተለዋለች ያሉትን ባህርይዋን የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሬክስ ቲለርሰን አወገዙ።
የእሥላማዊ መንግሥት ቡድንን ሽንፈት ተከትሎ ዩናይትድ ስቴትስ በአካባቢው ከሽብሩ ቡድን ጋር ሲፋለሙ ለነበሩ ቡድኖች ስትሰጥ የቆየችውን ድጋፍ እየቀነሰች መሆኗን ዋይት ሃውስ ትናንት አስታውቋል።
ተጨማሪ ይጫኑ