የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ከትናንት በስተያ ለተወካዮች ምክር ቤቱ ጥምር ጉባዔ ያደረጉት ንግግር በተከታተሉት አሜሪካዊያን በአመዛኙ አዎንታዊ አቀባበል ማግኘቱ እየተሰማ ነው። ፕሬዚዳንቱ በንግግራቸው ላይ መተባበርና የሁለቱንም ገዥ ፓርቲዎች የጋራ ውሣኔዎች መጠየቃቸው ብዙ ሪፐብሊካንን አስደስቷል።ዴሞክራቶቹ ግን በትረምፕ እውነተኛ አቋም ላይ ጥርጣሬአቸው እንደበረታ ነው።
ኢሚግራንቶች ለአሜሪካ ሸክም ሳይሆኑ ሃብት ናቸው ሲሉ የቴክሳሷ ዳላስ ውስጥ የምጣኔ ኃብት ምሁርና ፕሮፌሰር የሆኑት ዶ/ር መሐመድ ለአሜሪካ ድምፅ ገልፀዋል።
ላለፉት 18 ዓመታት አንድ ሥራ ላይ ያለ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት በዓለም የምጣኔ ኃብት መድረክ ላይ ሲሣተፍ የአሁኑ የመጀመሪያው ሊሆን ነው። Davos Elite Brace for Trump’s ‘America First’ Agenda
ላለፉት 18 ዓመታት አንድ ሥራ ላይ ያለ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት በዓለም የምጣኔ ኃብት መድረክ ላይ ሲሣተፍ የአሁኑ የመጀመሪያው ሊሆን ነው።
ወልድያ ውስጥ በጥምቀት በዓል ቀናት የመከላከያ ሠራዊት አባላት ናቸው በተባሉ ታጣቂዎች በተከፈተ ተኩስ የተገደሉ አባቶች የአድራጎቱ ተጠያቂዎች በአፋጣኝ ሕግ ፊት እንዲቀርቡላቸው ጠይቀዋል።
ወልዲያ ውስጥ የተፈጠረው የከተማዪቱን ማኅበራዊ ስብጥርና ግንኙነቶች የማያንፀባርቅ አሣዛኝ ሁኔታ መሆኑን በሰሞኑ ግርግር የንግድ ተቋማቸውና መኖሪያ ቤታቸው ሙሉ በሙሉ እንደወደሙባቸው የገለፁት የኃይላይ ሕንፃ ባለቤት አቶ ኃይላይ ንጉሤ ለቪኦኤ ገለፁ።
ዶ/ር መረራ ጉዲና ለአውሮፓ ፓርላማ እማኝነት የሰጡበትን መድረክ ካዘጋጁትና ከጋባዦችም አንዷ የነበሩት የፓርላማው አባል አና ጎምሽ የኢትዮጵያ መንግሥት 528 እሥረኞችን በመፍታቱ የተፈጠረውን ደስታ ከተጋሩት ሰዎች አንዷ ቢሆኑም የኢትዮጵያን መንግሥት በብርቱ ኮንነዋል።
በአማራ ክልል ወልድያ ከተማ ሲካሄድ በነበረው ሀይማኖታዊ ክብረ በዓል በተፈጠረ ግጭት ሰባት ሰዎች እንደተገደሉ ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ ሰዎች እንደቆሰሉ ተገለፀ፡፡
ምናልባት መንግሥቱን ነገ፤ ሰኞ ለመክፈት የሚያስችል ስምምነት ላይ ለመድረስ በሚል የሁለቱም ፓርቲዎች እንደራሴዎች ማምሻውን በር ዘግተው ስብሰባ ተቀምጠዋል።
በግጭቶቹ ቢያንስ የስድስት ሰው ሕይወት መጥፋቱን፣ የቆሰሉም እንዳሉ፣ በቁጥጥር ሥር የዋሉም እንደነበሩ የመላ ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አቶ አዳነ ጥላሁን ለቪኦኤ ገልፀዋል።
የኢሕአዴግን የሁለት ሣምንታት ግምገማ ተከትሎ እየተወሰዱ ባሉ እርምጃዎችና በሌሎችም አጠቃላይ ጉዳዮች ላይ የኢትዮጵያ የመንግሥት ኮምዩኒኬሽንስ ጉዳዮች ኃላፊ ሚኒስትር ዶ/ር ነገሪ ሌንጮ ለአሜሪካ ድምፅ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
ኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስና የመላ አማራ ሕዝብ ድርጅት ዓለምአቀፍ ድጋፍ ሰጭዎች በጋራ ለመሥራት ተስማምተው የመግባቢያ ሰነድ ቅዳሜ፣ ጥር 12/2010 ዓ.ም ከዋሺንግተን ዲሲ ወጣ ብሎ በሚገኘው ማርክ ሴንተር ሂልተን ሆቴል ውስጥ ይፈራረማሉ።
ከገዥው ፓርቲና ከመንግሥት የሚጠበቀው “የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ሊቀመንበር ዶ/ር መረራ ጉዲና መፈታት ሳይሆን ለሕዝብ ጥያቄዎች መልስ መስጠት ነው” ሲሉ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል አቶ ጥሩነህ ገምታ ከቪኦኤ ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ ተናግረዋል።
ወደ ኢጣልያ የሚገቡ ስደተኞችና ፍልሰተኞች ቁጥር እየቀነሰ የመጣ ይምሰል እንጂ ከፈረንሣይ ጋር በምትዋሰነው ውቢቱ ቬንቲሚግሊያ ከተማ ያለው ሁኔታ ግን የሚያሳየው እንደዚያ ዓይነቱን እውነት አይደለም።
የቀድሞውን የዚምባብዌ ፕሬዚዳንት ሮቤርት ሙጋቤን ባለፈው ዓመት ዘልፈሻል በሚል ታስራ የነበረችን የዩናይትድ ስቴትስ ዜጋ ክሥ አንድ የሃገሪቱ ፍርድ ቤት ውድቅ አድርጎ በነፃ አሰናብቷታል።
ኢትዮጵያ የትረምፕ አስተዳደር በኢየሩሣሌም ላይ ይፋ ያደረገውን አቋም ከሚያወግዙ የፀጥታ ጥበቃ ምክር ቤት አባላትና የመንግሥታቱ ድርጅት ጠቅላላ ጉባዔ ታደሚዎችም ጎን ቆማለች።
በኢትዮጵያ የታሪክ መዝገብ በሥነ-ጥበብ ምዕራፍ በሙዚቃው ገፅ ላይ ጎልተው ካሉ ስሞች አንዱ በረከት መንግሥትአብ ተብሎ ይነበባል።
ምዕራብ ሃረርጌ ዳሮ ለቡ ወረዳ ውሰጥ ዛሬ ተጣለ ሲሉ የአካባቢው ነዋሪዎች በገለፁት ጥቃት አንድ ሰው መገደሉ፣ አንድ ሰው መቁሰሉና ሰባ ግመሎች መዘረፋቸው ተገለፀ። የዞኑ የመንግሥት ኮምዩኒኬሽንስ ጉዳዮች ኃላፊ ግን ዛሬ ተፈጠረ የተባለውን ሁኔታ አስተባብለዋል።
ተጨማሪ ይጫኑ