የኢትዮጵያ መንግሥት በሙስናና ሰብዓዊ መብት ጥሰት ጠርጥርያቸዋለሁ ያላቸውን ሰዎች በቁጥጥር ሥር እያዋለ ይገኛል ይህ ጉዳይም መነጋገርያ ሆኗል። በዚህ ጉዳይ አስመልክቶ የአቋም መግለጫ ያወጣ የትግራይ ክልል መንግሥት የክልሉ ህዝብና መንግሥት የህግ ልዕልና እንዲሰፍን አበርትተው ይሰራሉ ብሏል። እንዲሁም በሙስናና ሰብዓዊ መብት ጥሰት እየታየ ያለ ሁኔታ አንድ ብሄር መሰረት እንዳያደርግ እንታገላለን ሲል ገልፅዋል፡፡
የብሄራዊ ብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ሜቴክ የቀድሞ ዋና ዳይሬክተር ብርጋዴል ጄነራል ክንፈ ዳኘው የብረታ ብረትና ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን የቀድሞ ዋና ዳይሬክተር ሜጀር ጀነራል ክንፈ ዳኘው በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር ዋሉ።
በአላማጣ ከተማ ከሁለት ሳምንት በፊት የተፈጠረውን ግጭት ተከትሎ የኢትዮጵያ ክልሎችን ከሚያገኛኙ አውራ መንገዶች አንዱ የሆነው የአላማጣ ቆቦ መስመር ዝግ ሆኖ ቆይቷል።
የትግራይን ክልል ከአማራ ክልል የሚያገናኘው አላማጣ ቆቦ መስመር ለተሽከርካሪዎች ከተዘጋ 4 ቀናት አስቆጥሯል። መንገዱ የተዘጋው በአላማጣ ከተማ የታሰሩ ሰዎች እንዲፈቱላቸው በጠየቁ የቆቦ ከተማ ወጣቶች ነው ተብሏል።
ልጆቻቸውን ወደ ትግራይ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሚልኩ በየትኛውም የሀገሪቱ ክፍል ያሉ ወላጆች ሥጋት እንዳያድርባቸው የክልሉ ርዕሰ - መስተዳድር ዶ/ር ድብረፅዮን ገብረሚካኤል አሳስበዋል፡፡
በአላማጣ ከተማ የተፈጠረውን አለመረጋጋት ተከትሎ መንግሥት የወሰደው የሐይል እርምጃ እንደሚኮንነው ዓረና ለሉዓላዊነትና ዴሞክራሲ ፓርቲ አስታወቀ።
በመቀሌ ማረምያ ቤት ልጆቻችን ሰብዓዊ መብታቸው በጣሰ ተይዘው ይገኛሉ ሲሉ የታራሚዎች ቤተሰብ ገልፀዋል።
ከ2500 በላይ የትግራይ ህዝብ ዴሞክራስያዊ ንቅናቄ /ደምህት/ ሰራዊት አባላት መንግሥት ያቀረበው የሰላም ጥሪ ተቀብለው በዛሬው ዕለት ወደ ኢትዮጵያ ገብተዋል።
13ኛ የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ድርጅታዊ ጉባዔ ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል ሊቀመንበር በማድረግ በዛሬው ዕለት ተጠናቋል።
የመስቀል በዓል በአስመራ ባሕቲ መስከረም አደባባይ፤ በመቀሌ ጮምዓ ተራራ ተከበረ፡፡
13ኛው የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ጉባዔ በዛሬው ዕለት በመቀሌ ተጀምሯል።
13ኛው የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ጉባዔ
በአዲስ አበባና አከባቢዋ በተፈጠረው ግጭት የዜጉች ሕይወት ማለፍ፣ የአካላና እንዲሁም የንብረት ጉዳት መድረሱ የሚወገዝ ተግባር ነው ሲል የዓረና ሉዓላዊነትና ዴሞክራሲ አስታወቀ።
ከ2 ሺህ በላይ የትግራይ ሕዝብ ዴሞክራስያዊ ንቅናቄ (ደምሕት) ሠራዊት አባላት፣ በቅርብ ጊዜ ወደ አገር ውስጥ ይገባሉ ሲሉ፣ የንቅናቄው ሊቀ መንበር አቶ መኮነን ተስፋይ ተናገሩ።
የትግራይ ክልል በሰላማዊ መንገድ ትግል ለሚያደርጉ ሁሉ ድጋፉን እንደሚሰጥ አስታወቀ። የክልሉ መንግሥት ይህንን ያስታወቀው በዛሬው ዕለት ወደ ኢትዮጵያ ለገቡ የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ሠራዊት አባላት አቀባበል ላይ በተደረገ ንግግር ነው።
ከሃያ ዓመታት በኋላ የኢትዮጵና ኤርትራ ድንበር በዛላንበሳ አቅጣጫ ሲከፈት ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂና ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አሕመድ ተገኝተው ነበር ሆኖም ግን ለህዝብ መልዕክት ሳያስተላልፉ ነው የተመለሱት፣ ይህ አጀንዳ መነጋገርያ ሆኗል፡፡
በኢትዮጵያና ኤርትራ ድንበር ዛላንበሳ አካባቢ ላይ የሁለቱ ሀገራት ሕዝቦች አዲስ ዓመትን በጋራ አከበሩ፡፡
ኢትዮጵያ “የባህር ኃይል እንዲኖራት ለማድረግ እንቅቃሴዎች ተጀምረዋል” ሲሉ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄነራል ሰዓረ መኮንን አስታውቀዋል።
ዛላንበሳ ድንበር ላይ በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል ተገንብቶ የነበረው አጥር ከሃያ ዓመታት በኋላ መፍረሱ ተገለፀ።
ተጨማሪ ይጫኑ