አጣዳፊ ተቅማጥና ትውከት /አተት/ በትግራይ ክልል ከሰኔ 2010 ዓ.ም ጀምሮ በወረርሽኝ ከተከሰተ በኋላ 1266 ሰዎች መታመማቸውና 10 ሰዎች ደግሞ መሞታቸው የክልሉ የጤና ቢሮ አስታውቋል።
የዓረና ለሉዓላዊነትና ዴሞክራሲ ፓርቲ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ባለፈው ቅዳሜ እና እሁድ መደበኛ ስብሰባውን አካሂዷል። በስብሰባውን የፓርቲው የስድስት ወራት አፈፃፀምና ወቅታዊ ሀገራዊ ፓለቲካዊ ሁኔታም መገምገሙን የፓርቲው የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አምዶም ገብረሥላሴ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል።
ከኢትዮጵያና ከኤርትራ አዋሳኝ አከባቢዎች የተውጣጡ ነዋሪዎች ዛሬን አብረው ለመዋል ቀደም ሲል ይዘውት በነበረ ዕቅድ መሠረት በሺሆች እንደሚቆጠር የተነገረ የራማና የአካባቢው ሰው መረብ ወንዝ ዳር ሲገኝ ከኤርትራዪቱ ክሳድ ዒቃ ኤርትራ ግን አለመገኘታቸው ታውቋል።
የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ ማዕከላዊ ኮሚቴ ከነሐሴ 18 እስከ 20/2018 ስብሰባ አካሂዷል።
የትግራይ ቴሌቭዥን ሥራ አስኪያጅ አቶ ብርሃኑ አባዲ ከሥልጣን ለማውረድ የተፈፀመው አሰራር ሕግ የጣሰ አካሄድ ነው ብለዋል ቪኦኤ ያነጋገራቸው ምሁራንና የመቀሌ ከተማ ነዋሪዎች።
ከ60 በላይ የትግራይ ክልል ራማ ከተማና አካባቢዋ ነዋሪዎች ትናንት መረብን ተሻግረው የኤርትራ ከተማ በሆነችው ክሳድ ዒቃ ከኤርትራውያን ጋር ውለው ተመልሰዋል።
ከ18 ቀናት በፊት የትግራይ ክልል መንግሥት ሳያውቀው ወደ መቀሌ ከተማ ገብተው የነበሩ 45 የፀረ ሽብር የፌደራል ፖሊስ አባላት ወደ መጡብት በዛሬው ዕለት ከተያዙበት ተለቀው ወደ አዲስ አበባ ተመልሰዋል።
ከአዲስ አበባ ወደ ሰቲት ሑመራ ከተማ የ68 ነጋዴዎች ንብረት ጭነው ይጓዙ የነበሩ ሁለት መኪኖች፤ ደባርቅ ከተማ ሲደርሱ ፖሊስ በቁጥጥር ሥር አውሎ ንብረቶቹን እንዲራገፍ አድርጓል ሲሉ ንብረት የተያዘባቸው ነጋዴዎች ቅሬታ አቀረቡ።
የትጥቅ ትግል ማቆሙን ከአንድ ወር በፊት ያስታወቀው የትግራይ ሕዝብ ዴሞክራስያዊ ንቅናቄ(ደምህት) አባላትና አመራሮች በትግራይ ክልል መጠተው በሰላማዊ እና ህጋዊ መንገድ እንዲሳተፉ የክልሉ መንግሥት ጥሪ አቀረበ።