ከድምፃዊት አለም ከበደ ጋር የተደረገ ቃለ ምልልስ (ክፍል ሦስት)
ከድምፃዊት አለም ከበደ ጋር የተደረገ ቃለ ምልልስ (ክፍል ሁለት)
የሶስት ልጆች እናት ናት። ፍቅርተ አዲስ ትባላለች፤ የፍቅር ዲዛይን ባለቤትና መስራች ናት። ልብስን ዲዛይን ማድረግና መስፋት ከልጅነቷ የምትተገብረው የትርፍ ጊዜ ስራዋ ነበር።
በወጣት ሴቶችና በኮምፒውተር ቴክኖሎጂ የነበረውን ክፍተት ለመሙላት በዩናይትድ ስቴትስ ኒውዮርክ ከተማ አዲስ የስልጠና ዕቅድ መተግበር ጀመረ።
የአለም አቀፉ የጤና ድርጅት (WHO) ከ200 ሚልዮን ለሚበልጡ በህፃንነታቸው ግርዛት ለደረሰባቸው ሴቶች የአካልና የስነአዕምሮ እንክብካቤ እንዴት ሊደረግላቸው እንደሚገባ ለመጀመሪያ ጊዜ መመሪያ አወጣ።
አጭር የሬድዮ ትረካ
የዩናይትድ ስቴይትስ ኢምባሲ በአዲስ አበባ የባህልና የፈጠራ ማዕከል ከፈተ።
በአይቮሪኮስት (Ivory Coast) ለረጅም ጊዜ በወንዶች ብቻ የተለመደውን የሙዚቃ ባንድ በወጣት ሴቶች የሙዚቃ ባንድ ለመስበር ቀላል አልነበረም። ቤላ ሞንዶ (Bella Mondo) በሚል ስያሜ የሚታወቀው የሴቶች የሙዚቃ ባንድ በአቢጃን ታዋቂ መጠሪያ ሆኗል።
አካለ ስንኩልነት፣ ድህነት፣ ከአየር ንብረት መዛባትና ከሚታረስ መሬት እጥረት ጋር በተያያዘ ከገጠር ወደ ከተሞች የነዋሪዎች ፍልሰት በጎዳና ላይ ለሚታየው የተረጂ ቁጥር መበራከት ዋነኞቹ ምክንያቶች ናቸው።
የዓለም የመገናኛ ብዙሃን ነጻነት ቀን በዛሬውለት ሲከበር፤ ኢትዮጵያና ኤርትራ ምንም እንኳን የጋዜጠኞች ይዞታቸው ቢለያይም “አፋኝ” መንግስታት መሆናቸው ነው የተስተጋባው። የአለም የመገናኛ ብሀን ነጻነት ቀን ከመከበሩ አስቀድሞ የጋዜጠኞች ይዞታና የመገናኛ ብዙሃን ነጻነት ሁኔታ የሚያሳስባቸው የመብት ተሟጋች ድርጅቶች የተለያዩ ዘገባዎችን አውጥተዋል።
የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት በስራ ላይ የሚገኘው የዲፕሎማሲ መምሪያ በ2015 መጨረሻ በርካታ ኢትዮጵያውያን ሃገራቸውን ጥለው በጅቡቲ ወደብ በሶማሊያና በሱዳን አቋርጠው ወደ የመንና መካከለኛው ምስራቅ አሁንም እየተሰደዱ እንደሚገኙ አስታውቋል።
በዩናይትድ ስቴትስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስትያናት በአሜሪካን ሃገር ተወልደው ላደጉ ትውልደ ኢትዮጵያውያን ከሃይማኖት ትምህርት በተጨማሪ የኢትዮጵያን ባህልና ታሪክ በማስተማር ከፍተኛውን ሚና በመጫወት ላይ ይገኛሉ።
አለም አቀፉ የስድተኞች ድርጅት UNHCR እንደዘገበው እ.አ.አ ከ2000 ዓ.ም ጀምሮ ከኤርትራ ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡት ኤርትራውያን ቁጥር እያደገ መጥቷል። አብዛኛዎቹ ስደተኞች ወደሌሎች ሃገሮች ጥገኝነት ለመጠየቅና ለማግኘት ነው አመጣጣቸው።
በፍራንክፈርት ጀርመን ለሚገኙት ኢትዮጵያውያን አሮን ጌታቸውአስቂኝ ቀልዶቹን ሲያቀርብ።
አሮን ጌታቸው ይባላል። የ17 አመት ወጣት ነው። የመድረክ ተዋናይና የቀልድ ሰው መሆን ይፈልጋል። የሚኖረው ከኢትዮጵያ ርቆ ቢሆንም ኢትዮጵያዊ በመሆኑ ብቻ ደስታው የላቀ ነው።
አለም ከበደ ለየት ባለው የአዘፋፈን ስልቷ ትታወቃለች። ከዚህ ቀደም ሦስት የሙዚቃ አልበሞችን ሰርታለች። በቅርቡም አራተኛዋ የሆነውን የሙዚቃ አልበም ለአድማጭ አቅርባለች። ከሙዚቃ ህይወት ባትርቅም አዳዲስ ስራዎች ለመስራት ረጅም ጊዜ ወስዶባታል።
ኮሎምቢያዊው አንቶኒዮ (ቶኒ) አኮስታ (Tony Acosta) የጊታር ክር በማምረትና በመሸጥ ነው የሚተዳደረው። በርካታ ገንዘብን ከሽያጩ ካጠራቀመ በኃላ የራሱን ምርት የሚያስተዋውቅበትና የሚሸጥበትን መደብሮች በማንሃታን (Manhattan) ከፍቷል። ከዚህ ቀደም እንደሰማናቸው ከስኬት ጀርባ ያሉ የስራ ጥረቶች አሜሪካኖቹ እንደሚሉት አሜሪካን ድሪም “American dream” በህይወት ትግል ውስጥ አልፏል አኮስታ።
85 በመቶ የሚሆነው የኢትዮጵያን አርሶ አደርና አርብቶ አደር የዝናብ ውሃን ጠብቆ ነው የሚተዳደረው። በየአመቱ በሚዘንበው የዝናብ መጠን ማነስ ከአምራች ገበሬዎቹ ህይወት በተጨማሪ በምግብ አቅርቦት ላይ ከፍተኛ እጥረት ይገጥማል።
ሳሙአል መርጋ ይባላል። እድሜው 17 ሲሆን የ12ኛ ክፍል ተማሪ ነው። ነዋሪነቱ በአዲስ አበባ ቦሌ ሚካኤል ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነው። በመደበኛ ትምህርቱ የከፍተኛ ውጤት ተሸላሚ ነው።የተለያዩ ቅርፅ ያላቸው ትንንሽ ተንቀሳቃሽ ሮቦቶችን ሰርቷል በመስራትም ላይ ይገኛል።
ተጨማሪ ይጫኑ