ሳሙአል መርጋ ይባላል። እድሜው 17 ሲሆን የ12ኛ ክፍል ተማሪ ነው። ነዋሪነቱ በአዲስ አበባ ቦሌ ሚካኤል ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነው። በመደበኛ ትምህርቱ የከፍተኛ ውጤት ተሸላሚ ነው።የተለያዩ ቅርፅ ያላቸው ትንንሽ ተንቀሳቃሽ ሮቦቶችን ሰርቷል በመስራትም ላይ ይገኛል።
በርካታ ሰዎች በተለያዩ መዝናኛ ቦታዎች በሚገኙ በፍጥነት ከፍና ዝቅ እያሉ በሚምዘገዘጉ ተሽከርካሪ መሰል የሮለር ኮስተርስ (Roller Coasters) ይዝናናሉ። ለአዲሱ ትውልድ በአዲስ ቴክኖሎጂ የተሰራው Roller Coasters በምናብ የሚያሳዩ ታምራዊ የእይታ ቴክኖሎጂዎች ተገጥሞላቸዋል። በአሁኑ ሰዓት በሰሜን አሜሪካ በሚገኘው ቲም ፓርክ (Theme Park)፣ በአውሮፓና በእስያ አዲሶቹ የቴክኖሎጂ ግኝቶች በግልጋሎት ላይ ውለዋል።
እ.አ.አ 1985 ዓ.ም በተሰራው የሆሊውድ ፊልም ባክ ቱ ዘ ፊውቸር “Back to the Future” ለማሳየት የሞከረው የወደፊት ቴክኖሎጂ እውን የሆነ ይመስላል። በፊልሙ ውስጥ ማርቲ ማክፍላይ (Marty McFly) በማክል ጄ ፋክስ (Michael J. Fox) የተተወነው ገፀባህሪ የሚለብሰው ጫማ ራሱን በራሱ እግር ፈልጎ ጥልቅ ይልና፤ ያስርም ነበር።
ሳልሳ የሙዚቃ ስልት ስረ መሰረቱ ከኩባና በውሃ ከተከበበችው ደሴት ፖርተሪኮ ነው። የሳልሳ ሙዚቃ ለነዚህ ሁለት ሃገሮች መገለጫቸው የሆነ የባህላዊ የዳንስ ሙዚቃ ነው።
ዓለም አቀፉ የጤና ድርጅት WHO ባደረገው ጥናት መሰረት በአለማችን ከሚከሰቱት ድንገተኛ ሞት በአመት 12.6 ሚልየን የሚሆነው ጤናማ ባልሆኑ የአካባቢ ንብረት መበረዝ ምክንያት እንደሆነ ተረጋግጧል።
ማይክሮሶፍት የተባለው አለም-አቀፍ የኤሌክትሮኒክስ አምራች ኩባንያ ባሳለፍነው የፈረንጆቹ አመት እ.አ.አ 2015 ዓ.ም ቅርንጫፍ መስሪያ ቤት “ማይክሮሶፍት ፎር አፍሪቃ” በሚል ስያሜ በናይሮቢ ኬንያ ከፍቷል።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በዋሽንግተን ዲሲ ሜሪላንድና ቨርጅኒያ ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የሃገርን ቅርስ ባህልና ታሪክ በማስጠበቅና በማሳወቅ ከፍተኛ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ ይገኛል።
“የመገናኛ ብዙሃን ለቋንቋ እድገትም ሆነ መቀጨጭ አስተዋፆ አለው፡ ጋዜጠኛም ሆነ ፀሃፊ በቋንቋው ላይ ጥንቃቄ ሊያደርግ ይገባዋል” ይላል እንግዳችን አቤል አዳሙ።
ከተመሰረተ ከአራት አመት ተኩል በላይ የሆነው የጃኖ ባንድ አራት ድምፃውያንና ስድስት የሙዚቃ መሳሪያ ተጫዋቾች የያዘ ነው።
እንግሊዛውያኑ ወጣት ሮሊንግ ስቶንስ (Rolling Stones) እ.አ.አ በ1960ዎቹ በሮክ ኤንድ ሮል (Rock & Roll) የሙዚቃ ስልት የተለየ አድማጭ ያገኙ ተወዳጅ ሙዚቀኞች ነበሩ።
የጅቡቲ መንግስት ከኢትዮጵያና ከቻይና ጋር ያደረገችው የነዳጅ ፍለጋ ግንባታ ስምምነት በምስራቅ ኢትዮጵያ የሚገኙትን የሱማሊያ አማፂ ቡድን አስቆጣ።
በ1960ዎቹ ሴት ልጅ በአደባባይ መውጣት ባልተለመደበት ዘመን ፤ ደስታ ሃጎስ የራስዋን የስዕል ኤግዚቢሽን በኢትዮጵያ ያዘጋጀች የመጀመሪያዋ የሴት ሰአሊ። ባሳለፈችው የጥበብ ስራ ዘመን ከሃምሳ ጊዜ በላይ የስዕል ኤግዚቢሽኖችን ለብቻዋና ከሌሎች ሰአሊዎች ጋር በጋራ በመሆን ለእይታ አቅርባለች።
የአለም አቀፉ የጤና ድርጅት WHO 60 በመቶ የሚሆነው መስማት የተሳናቸው ሕፃናትን ችግር ለመከላከል የሚያስችል አዲስ ጥናት እንደተገኘ አስታውቋል። በዛሬው እለት በሚከበረው አመታዊ “የመስማት ቀን” ህፃናት የሚያጋጥማቸውን የጆሮና የመስማት ችግር እንዴት መከላከል እንደሚቻል WHO ሲወያዩበት ቆይተዋል።
የዩናትድ ስቴትስ የጠቅላይ ፍርድቤት ግዙፉን የአፕል ኩባንያ በሳንበርዲኖ ለደረሰው የአሸባሪዎች ጥቃት ምርመራ ትብብር እንዲያደርግ ጠየቀ።
በኢትዮጵያ ከተሞች በተለይም በመዲናችን በአዲስ አበባ አንድ የተለመደ ግን ትክክል ያልሆነ ልምድ አለ። ሰውን ያለአግባብ በቃላት መዝለፍ፣ መስደብ ከዛም ባለፈ የሰውነት ትንኮሳ፤ በተለይ በሴቶች ላይ።
ሐምራዊት ተስፋ “ልጅን ማሳደግ በምዕራብ ሃገሮች” የተሰኘ ኢትዮጵያዊነቱን ሳይለቅ ከአሜሪካ ባህል ጋር አጣጥሞ ልጅን እንዴት ማሳደግ እንደሚቻል መፅሃፍ በማሳተም በአሜሪካን ሀገር ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ወላጆች አቅርባለች።
አስመራ በዩኔስኮ UNESCO የአለም ታሪካዊ ስፍራዎች ወይም “World Heritage”፤ ህንጻዎቿን፣ ታሪኳን እና የግንባታ ውበቷን ልትመዘገብ እጩ ሆናለች።
አምበር ስታይም የተወለደችው በጎንደር ደብረታቦር ከተማ ነው። የ3 አመት ልጅ እያለች ከመሬት መጫወቻ መስሏት ያነሳችው ቦንብ ፈንድቶ ሁለት እጆቿን አሳጥቷታል።
ሳራ ነጋሽ ወደ አሜሪካን ሃገር መኖር ከጀመረች አመታትን አስቆጥራለች። በማደጎነት ወደ አሜሪካ ያመጣቻት አሜሪካዊት እናት ሳራ እንዳሰበቻት መልካም ወላጅ ልትሆንላት ስላልቻለች በሊሎች ፈቃደኛ ወላጅ አሳዳጊዎቿ ቤት መኖር ጀምራለች። "አሁን ያለሁበት ቤት ውስጥ ደስተኛ ነኝ" ትላለች ሳራ።
“Young Ethio-jazz Band” በሚል ስያሜ ይታወቃሉ። ተወልደው ያደጉት በዩናይትድ ስቴትስ ኦክላንድ ካሊፎርኒያ ነው። እድሜያቸው ከዐስራ ሦስት እስከ ዐስራ ስምንት የሆኑት አነዚህ ወጣቶች በጋራ ሙዚቃን መጫወት የጀመሩት የዛሬ አራት ዓመት ነው።"ኢትዮጵያዊነታችሁን ለማስተዋወቅ አትፈሩ" ይላል ከሙዚቃ ባንድ አባላት አንዱ።
ተጨማሪ ይጫኑ