ዛሬ በእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ የኢድ አድ አልሃ በዓል ተከብሮ ውሏል።
የሼ ቅቤ በአለም አቀፍ ከዉበት መጠበቂያ እስከ ምግብ ግልጋሎት ተወዳጅ የሆነ የተፈጥሮ ቅባት ነው። ከሼ ዛፍ የሚገኘው ፍሬ የሴቶች ወርቅ በመባል ይሞገሳል በአይቮሪኮስት፤ በሳህል መንደር ለሚኖሩ በርካታ ሴቶች የገቢ ምንጭ በመሆኑ ነው ይህ ስያሜ የተሰጠው። በሰሜናዊው አይቮሪኮስት የሼ ቅቤን ከጎጆ ኢንደስትሪ ወደ ከፍተኛ ንግድ ለመለወጥ ከፍተኛ እንቅስቃሴ በመደረግ ላይ ነው። ለሙሉ ዘገባው ተንቀሳቃሽ ምስሉን በመጫን ይመልከቱ።
ኢትዮጵያዊያን በዩናትድ ስቴይትስ ለትምህርት በሚመጡ ጊዜ የሚገጥሟቸው ፈተናዎችና እድሎች አሉ። ሜሮን ፋሲካ ዲቢያ በኦሃዮ ስቴይትስ ዩኒቨርስቲ በፊዚክስ የከፍተኛ ትምህርት (PHD) ተማሪ ናት።
በቲምቡክቱ በሚገኙ ተወዳጅ እድሜ ጠገብ ሃውልቶች ላይ ባደረሰው ውድመት በአለም አቀፉ ፍርድ ቤት ታሪክ የመጀመሪያ በሆነው የቅርስ ማጥፋት ወንጀል የጅሃድ አራማጁ አህመድ አልፋቂ አልማህዲ ተከሰሰ።
በመደበኛ ሥርጭታችን ያልተካተቱ ዘገባዎችን የሚጨምር የአፍሪካ አበይት ዜናዎች - ሐምሌ 21 2008
በመደበኛ ሥርጭታችን ያልተካተቱ ዘገባዎችን የሚጨምር የአፍሪካ አበይት ዜናዎች ቅንብር - ሐምሌ 20 2008
በመደበኛ ሥርጭታችን ያልተካተቱ ዘገባዎችን የሚጨምር የአፍሪካ አበይት ዜናዎች ቅንብር - ሐምሌ 19 2008
የወባ ትንኝ በከፍተኛ ሁኔታ የሚራባበት ቦታ ይኖሩ ከሆነ ዶሮዎችን ከመኝታዎ አጠገብ አድርጎ መተኛቱ ያዋጣል የሚል ጥናት በቅርቡ ተሰምቷል። የዶሮ የተፈጥሮ ጠረን የወባ ትንኝን አርቆ የሚያበር ሆኗል። ይህ ጠረን በወባ ምክንያት የሚከሰተውን ህመምም ለመከላከል ታላቅ አስተዋፆ እንዳለው በጥናቱ ተደርሶበታል።
ኤች አይ ቪ ኤድስን ለመከላከል የሚረዳ መድሃኒት ለማግኘት አበረታች ሳይንሳዊ ጥናቶች መኖራቸው፤ የፈውስ መድሃኒትን ለማግኘት የተያዙ ምርምሮችና፤ የቫይረሱን መቋቋሚያ እንክብሎች ቫይረሱን ለመከላከል ማስቻላቸው፤ በዚህ ሳምንት በደቡብ አፍሪካ ደርባን እየተካሄደ በሚገኘው አለም አቀፉ የኤድስ ጉባዔ አትኩሮት የተደረገባቸው ጉዳዮች ሆነዋል።
ከትላንት በስትያ በደቡብ አፍሪካ ደርባን በተጀመረው አለም አቀፉ የኤድስ ጉባዔ ላይ ቫይረሱን ለመከላከል የሚያስችል አዲስ የመድሃኒት ግኝት ይፋ ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል። ጉባዔው ቫይረሱን በመከላከልና በመቆጣጠር ዙሪያ ምን እንደተሰራ ይገመግማል፤ ለመጪዎቹ አምስት አመታት ሊተገበሩ የሚገባቸውን አዳዲስ እቅዶችንም ያወጣል።
ህፃናትን ከቫይረሱ በመከላከል ዙሪያ በሰፊው በመሰራቱ እ.አ.አ በ2001 ዓ.ም ከተመዘገበው የሕፃናት የመያዝ ቁጥር 70 በመቶ ቀንሶ ታይቷል። በኤች አይ ቪ የተያዙ አዳዳዲስ አዋቂዎች ላይ በተደረገው ጥናት ግን በ2010 ዓ.ም ከተመዘገበው ቁጥር ጋር ሲተያይ ምንም አይነት ለውጥ አላሳየም። ለአምስት አመታት ቁጥሩ 1.9 ሚልየን ላይ ቆይቷል።
በኢትዮጵያ የዘንድሮው ሀገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በመሰጠት ላይ ይገኛል። ስለፈተናው ሁኔታ በምዕራብ ሐረርጌ፣ በጅማ ፣ በሻሸመኔ እና በአዲስ አበባ ተፈታኞች ስለፈተናው አጭር አስተያየታቸውን አድርሰውናል።
የዘንድሮው የኢድ አልፈጥር በዓል በደማቅ ሁኔታ በአስመራ ከተማ ተከብሮ ውሏል። በአስመራ ከተማ ነዋሪ የሆኑ ስለ በዓሉ አከባበር በአጭሩ ነግረውናል።
በዩናይትድ ስቴትስ ሎሳንጀለስ የጥቁር ሴቶች ጤንነት ላይ የሚሰራው (black women's wellness) የተሰኘው የግብረ ሰናይ ድርጅት አዲስ ዘገባ እንደሚያመለክተው፣ ለጸጉር ማስዋቢያ ከሚቀመሙት ንጥረ ነገሮች ውስጥ ለሴቶችና ለአዳጊ ሴቶች ለማህፀን ጤና አስጊ የሆኑ ንጥረ ነገሮች እንደሚገኙበት ዘግቧል። እነዚህ ንጥረ ነገሮች የፀጉር ማፍታቻ (Relaxer)፣ የፀጉር ሳሙና (Shampoo) እና የፀጉር ቀለሞች ለጤና ከፍተኛ ጉዳት ያላቸው መሆናቸው ተደርሶበታል።
ታላቋ ብሪታንያ በዋናነት ታስተዳድራቸው ከነበሩት 13 ግዛቶች ውስጥ ዩናይትድ ስቴትስ እ.አ.አ በጁላይ 2 1776 ነጻ ወጣች። ይህ አመታዊ ታላቅ በአል የበጋ ወቅት ላይ በመሆኑም ቤተሰብ ዘመድ አዝማድ እንዲሁም ጓደኛ የሚገናኝበትና በጋራ የሚከበር በዓል ነው። ነዋሪነታቸው በዚህ በዩናይትድ ስቴትስ የሆኑ ጥቂት ኢትዮጵያውያንን በአሉን እንዴት እንደሚያከብሩ በአጭሩ ነግረውናል። ከበታች ያለውን የድምፅ ምልክት በመጫን ያድምጡ።
"በህገወጥ መንገድ ስደተኞችን ከሃገር ወደ ሃገር በማስተላለፍ ወንጀል ተጠርጥሮ የተያዘው ግለሰብ በወንጀለኝነት የሚፈለገው ትክክለኛው ሰው አይደለም" የሚሉ ድምፆች እየተሰሙ ነው። ተጠርጣሪውን መከታተልና በቁጥጥር ስር በማዋሉ ስራ የተሳተፉት የብሪታንያንና የጣልያን የደህንነት ባለስልጣናት በበኩላቸው በጉዳዩ ላይ አስቸኳይ ምርመራ መያዛቸው ተዘግቧል።
ከአሜሪካ ማህበረሰብ ራስን መግለጽ ጥቅሙ ምን ያህል እንደሆነ እንማር! ምናልባት ለአይናፋር ሰዎች ስለራስ መናገር ይከብድ ይሆናል። የስነልቦና ተመራማሪዋ ሱሳን ኬይን ስለራስዋ ገልፃ መናገር ባትችልም ለመሰሎቿ ራሳቸውን በሰዎች ፊት መግለፅ ለማይችሉት፤ ተሟጋች ሆና ቀርባለች።
በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች የሚኖሩ የዘንድሮ ተፈታኝ ተማሪዎች አስተያየት የሰጡን ለምሽቱ ተካቷል።
በጀርመን ፍራንክፈርት ከተማ ቁጥራቸው ከፍተኛ የሆነ ኢትዮጵያውያን ይኖራሉ። ታድያ ከሀገር ርቀው እንደመኖራቸው ኢትዮጵያዊነታቸውን እንዳይረሱ ወላጆች ለልጆቻቸው የኢትዮጵያን ታሪክ፣ ባህልና ቋንቋ ለማስተማር ይጥራሉ።
የፈተናው ትናንት መቋረጥ አዲስ አበባ ውስጥ ላሉ ተፈታኞች አሣዛኝ መሆኑን ቪኦኤ ያነጋገራቸው አስረድተዋል፡፡
ተጨማሪ ይጫኑ