የድምፃዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ የቀብር ሥነ ስርዓት ዛሬበተወለደባት አምቦ ከተማ ገዳመ ኢየሱስ ቤተ ክርስቲያን ተፈፅሟል። የሽኝት ሥነ ስርዓቱ በአምቦ ዩኒቨርስቲ ስታዲየም ተከናውኗል። በሥነ ስርዓቱ ላይ በፀጥታ ስጋት ምክኒያት ቁጥሩ አነስተኛ የሆነ ሰው መገኘቱን ታላቅ ወንድሙ አቶሃብታሙ ሁንዴሳ ገልፀውልናል።
“የልጄን ደም ያፈሰሱትን ሰዎች መንግሥት ሕግ ፊት እንዲያቀርብልኝ እፈልጋለሁ” ሲሉ ሰኞ ዕለት እስካሁን ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች በተተኮሰ ጥይት የተገደለው ታዋቂው የኦሮሚኛ ቋንቋ ድምፃዊ ሃጫሉ አባት አቶ ሁንዴሳ ቦንሳ ተናገሩ።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከትግራይ ክልል የቀረበለትን የምርጫ ማካሄድ ጥያቄበሁለት ምክኒያቶች እንደማይቀበለው በዛሬው ዕለት ባወጣው መግለጫ ይፋ አድርጓል።
የዝናብ እና ፀሐይ ላይ ተቃውሞ
የዕድር ጡሩምባም ነበር
የጥቁር አሜሪካዊው ጆርጅ ፍሎይድ ሞት ተከትሎ በቀሰቀሰው ተቃውሞ በዋሽንግተን ዲሲ ኋይት ሃውስ ቤተመንግሥት አቅራቢያ የነበሩ በጎ ፈቃደኞችን ያነጋገረችው ጽዮን ግርማ ያሰናዳችውን የምስል ዘገባ ተከታተሉ።
የአምነስቲ ኢንተርናሽናል የአፍሪካ ቀንድ የሰብዓዊ መብቶች ጉዳዮች አጥኚ ጋር የተደረገ ቃለ ምልልስ
በኮሮና ቫይረስ ምክኒያት በእንቅስቃቄ ላይ ገደብ ከተጣለ በኋላ በትምሕርት እና በሕክምና ምክኒያት ሕንድ ውስጥ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በየዕለቱ ተደራራቢ ችግር እየደረሰባቸው መሆኑን ገለፁ። 16 የሚሆኑ ተማሪዎች ፤ ከሙምባይ የሚደረግ ልዩ በረራ እንደሚኖር ሰምተው 36 ሰዓት በመኪና ተጉዘው ሲደርሱ፤ የተባለውን ባለማግኘታቸው ለከፍተኛ ችግር መዳረጋቸውን ተናግረዋል።
በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክኒያት በገቢያቸው ላይ ተፅዕኖ ያሳደረባቸው በአፍሪካ ቀንድና በታላላቅ ሐይቆች አካባቢ ከተሞች ውስጥ የሚኖሩ በመቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ስደተኞች ተስፋ ወደ መቁረጥ እያመሩ እንደሆኑ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የስደተኞች ጉዳዮች ከፍተኛ ኮሚሽነር (ዩ.ኤን.ኤች.ሲ.አር) ማስጠንቀቂያ አውጥቷል።
የገዢው ፓርቲ እጩ የብሩንዲን ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ በአብላጫ ድምፅ ማሸነፋቸው እስካሁን ይፋ በሆነው ውጤት እየተነገረ ነው። በሌላ በኩል የተቃዋሚ ፓርቲዎች “የምርጫው ውጤት ተጭበርብሯል” በማለት አቤቱታ እያሰሙ ይገኛሉ።
ዩናይትድ ስቴትስ ባካሄደቻቸው ጦርነቶች ለአገራቸው የተሰው በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎቿን፤ ዛሬ ሰኞ “ሚሞሪያል ዴይ” በሚል በተሰየመው የመታሰቢያ ቀን እያሰበቻቸው ትገኛለች። እነዚህን ለአገራቸው የወደቁ አርበኞችን ለማሰብም በመላ አገሪቱ ባንዲራ ዝቅ ብሎ እንዲውለበለብ ተደርጓል።
ሜሪላንድ ውስጥ ነዋሪ የነበሩ የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን አገልጋይ በኮሮናቫይረስ መያዛቸው ፤ ከዚያም ውጤታቸው ነፃ መሆናቸውን ካሳየ በኃላ ሕይወታቸው አለፈ። ኃኪሞቻቸው ቫይረሱ ከውስጣቸው ቢጠፋም በውስጥ አካላቸው ላይ አድርሶባቸው ከሄደው ጉዳት ማገገም እንዳልቻሉ ለቤተሰቦቻቸው ነግረዋቸዋል። ወንጌላዊ ወሰንየለው ሳህሌ የአራት ልጆች አባት ነበሩ። ባለቤታቸውን አነጋግረናል።
ከኮሮና በፊትም እልክ ነበር፣ አሁን በኮሮና ጊዜም እልካለሁ ፣ ከኮሮና በኋላም መላኬን እቀጥላለሁ - (ቪዲዮውን ይመልከቱ)
“እርሷ ለልጆቿ ሕይወቷን እንደሰጠች እኔም እሰጥላታለሁ። ልጆቹን ሰብስቤ አሳድግላታለሁ” - የ17 ዓመቷ የወገኔ ልጅ
“ክፉ ቀን ሲያልፍ የሚመጥነው መታሰቢያ እናዘጋጅለታለን” - የቴዲ ጓደኞች
በኢትዮጵያ የሚገኙት አብዛኞቹ የኮሮና ቫይረስ ታማሚዎች ኤካ ኮተቤ ሆስፒታል ተኝተው ይገኛሉ። የሆስፒታሉን ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ዳዊት ኪዳኔ ሆስፒታሉ ስላለው አቅምና ተያይዥ ጉዳዮች በሚያዚያ 3/ 2012 ዓ.ም ተጠይቀው የሰጡት ምላሽ በዘገባው ተካቷል። የመጀመሪያዋ ሟች አስክሬን በድጋሚ ስለመቀበሩም ሁኔታ ጠይቀናቸዋል። ዘገባውን አዳምጡት።
በሳውዝ ዳኮታ በኮሮናቫይረስ የተያዘች እናትና ስታስታምማት ከቆየች ልጇ ጋር የተደረገ የስካይፕቃለ ምልል።
ወ/ሮ ወገን ደበላ በሜሪላንድ ታኮማ ፓርክ በተባለ ቦታ ነዋሪ ነበረች። “ልጆቿን በትና ጥላኝ ሄደች” ያሉን ባለቤቷ አቶ ይልማ አስፋው ደግሞ የትምሕርት ቤት አውቶብስ አሽከርካሪ ናቸው። ቤታችን ውስጥ እጅግ የመረረ ሐዘን ገብቷል ያሉት አቶ ይልማ የተወለደው አራስ በ17 ዓመቷ ልጃቸው እቅፍ ውስጥ እንደሚገኝ ገልፀዋል።
ተጨማሪ ይጫኑ