በደቡብ አፍሪካ - ፕሪቶርያ በተደረሰው፣ ግጭትን በዘላቂነት የማቆም የሰላም ስምምነት መሠረት፣ ከፌዴራሉ መንግሥት ጋራ የፖለቲካ ውይይት በአፋጣኝ እንዲጀመር፣ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ጠየቀ፡፡ ጥያቄው፣ ለአፍሪካ ኅብረት አደራዳሪ ቡድንም እንደቀረበና ምላሽ እየተጠበቀ እንደኾነ፣ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ጽሕፈት ቤት ሓላፊ አቶ ዐማኑኤል አሰፋ፣ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል፡፡