ታቲያና ክፍሌ ነዋሪነቷን በዩናይትድ ስቴትስ ያደረገች የስድስት የህጻናት መጽሃፍት ደራሲ እና በርከት ያሉ የህጻናት ሙዚቃዎች አዘጋጅ ናት። በተከታታይ ለአንባቢያን ባቀረበቻቸው መጽሃፍት ትውልደ -ኢትዮጵያዊያን ህጻናት ከባህላቸው ጋር እንዲተዋወቁ፣ የወላጆቻቸውን የአፍ መፍቻ ቋንቋ እንዲለምዱ በማገዝ ላይ ትገኛለች። ሀብታሙ ስዩም በቅርቡ በተደረገው "ቴስት ኦፍ አፍሪካ " ትርዒት ላይ ታቲያናን አግኝቶ ከስራወቿ ጋር የተገናኙ ጥቂት ጥያቄዎችን አቅርቦላታል።
የኢትዮጵያዊያን አዲስ ዓመት በመላው ዓለም በሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ዘንድ በድምቀት ተከብሯል። በዋሺንግተን ዲሲ፣ ሜሪላንድ እና ቨርጂኒያ አካባቢዋ የሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያዊያን በዓሉን በማስመልከት ካዘጋጇቸው ትርዒቶች አንዱ "እንቁጣጣሽ ፌስቲቫል " ይሰኛል።ፌስቲቫሉ በተካሄደበት አሌክሳንድሪያ ከተማ የተገኘው ሀብታሙ ስዩም ከፌስቲቫሉ አዘጋጆች እና ተሳታፊዎች ጋር ቆይታ አድርጓል።
የስነ -ህንጻ ባለሙያ የሆነችው ህሊና ተክሉ ፣ በማህበራዊ ተሳትፎ እና አየር ንብረት ጥበቃ አንቂነት እንቅስቃሴዊቿ ዕውቅናን እያገኘች የመጣች ወጣት ናት። ህሊና የበለጠ ትኩረት እንድታገኝ ያደረጋት የኢትዮጵያን የግብርና መልክ የመቀየር ዓለማ ያለው የተለያዩ አዝዕርት እና ዛፎችን ዘሮች ከዳበረ አፈር ጋር ቀላልቅሎ በትንሽ ኳስ መሳይ ቅርጽ ለተጠቃሚዎች በሚያቀርበው ሲድ ቦል" የተሰኘ ድርጅት መመስረቷ ነው። ስለ ድርጅቱና እና ተያያዥ ጉዳዮች ሀሳቦቿን አካፍላናለች ።
ህጻናት እና ወጣቶች የክረምቱን መገባደድ የአዲሱን ዘመን መቃረብ በጭፈራ እና በዝማሬ ከሚያበስሩባቸው በዓላት መካከል አንዱ "ቡሄ" ነው። ይህ ባህላዊ እና ኃይማኖታዊ መሰረት ያለው በዓል ከእነወዘናው ዓመታትን ይሻገር ዘንድ ለወጣቶች ስልጠና እና ድጋፍ ከሚያደርጉት መካከል አንዱ መምህር አቤል ተስፋዬ ናቸው ። ዘማሪ፣ የበገና አደራደር እና ክራር ባህላዊ መሳሪያ አስተማሪ የሆኑት መምህር አቤል ስለ ቡሄ በዓል ፣ዝማሬዎች እና ተያያዥ ጉዳዮች ሀሳባቸውን ያቀብሉናል።
ተማሪ ቤት ተማሪዎች ስለ ሚማሩት ነገር በቂ ዕውቀት እንዲኖራቸው በማስቻል ፣ የኢትዮጵያን ትምህርት አሰጣጥ ለማዘመን ያለመ ተቋም ነው። ተቋሙ ከፊት ለፊት ጥናት አገልግሎት በተጨማሪ ፣ በዲጂታል የቪዲዮ እና የጽሁፍ ማስተማሪዎች ለአንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ዕውቀትን ያዳርሳል። ስለ ተማሪ ቤት የበለጠ ለማወቅ ሀብታሙ ስዩም የአገልግሎቱን መስራች ሀብታሙ አሰፋን አነጋግሯል ።
በኮሎምቢያ ካሊ ለአንድ ሳምንት ሲደረግ የሰነበተው የዓለም ከ20 ዓመት በታች አትሌቲክስ ቻምፒዮና ተጠናቋል። የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን የዩናይትድ ስቴትስ እና ጃማይካ አትሌቲክስ ቡድኖችን በመከተል በ6 ወርቅ 5 ብር እና 1 ነሃስ ሜዳሊያ ከዓለም ሶስተኛ ደረጃን ፣ ከአፍሪካ ደግሞ የአንደኛ ደረጃን ይዞ አጠናቋል። የቡድኑ ድል ስለ ፈጠረው ስሜት እና በተተኪ ወጣቶች ዘንድ ስለሚኖረው ፋይዳ ለመረዳት የቡድኑን መሪ አትሌት መሰለች መልካሙን አነጋግረናል።
"ታስክ ሞቢ " ብዙም ትኩረት ባላገኙ የስራ መስኮች ላይ የተሰማሩ ወጣቶች ፣ ተገቢውን የስራ ክብር እና ከፍያ እንዲያገኙ ለማድረግ ያለመ የቴክኖሎጂ ተቋም ነው። ከመንግስታዊ እና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ጋር በመተባበር የቤት ጽዳት፣ ቧንቧ ዝርጋታ ፣ የቀለም ቅብ ስራዎች እና በመሳሰሉት አገልግሎቶች የተሰማሩ ወጣቶችን ከአገልግሎት ፈላጊዎች ጋር በስልክ መተግበሪያ እና ቀጥታ ጥሪ አውታሩ በኩል ያገናኛል።ዘገባው ከስር ተያይዟል።
ኦሪገን -ዩጂን ላይ ሲደረግ በሰነበተው 18ኛው የዓለም አትሌቲክስ ቻምፒዮና ላይ ከተወዳዳሩ የዓለም ሀገራት መካከል የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን ፣ የዩናይትድ ስቴትስ አትሌቲክስ ቡድንን በመከተል ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቋል።ይሄ ድል ለስፖርቱ እና ከስፖርቱ ባሻገር ስላለው ፋይዳ ለማወቅ የአትሌቲክስ ቡድኑን መሪ አቶ ተፈራ ሞላን ጠይቀናል።
መዝገበ -አዕምሮ የ180 ኢትዮጵያዊያን የሚዲያ ሰዎችን ፍኖተ-ሙያ የሰነደ አዲስ መጽሃፍ ነው።የአንጋፋ እና ወጣት ጋዜጠኞችን ታሪክ በተገቢው መንገድ በማሰባሰብ ለቀጣዩ ትውልድ የማሸጋገር ግብ እንዳለው የተነገረለትን መጽሃፍ ዝግጅት ያስተባበረው ተወዳጅ ሚዲያ እና ኮሚዩኒኬሽን የተባለ ድርጅት ነው። ስለ መጽሃፉ ዝግጅት እና ፋይዳ ለማወቅ የድርጅቱን ኃላፊ ጋዜጠኛ እዝራ እጅጉን አነጋግረናል ። መጽሃፉን ማሳተም አስፈላጊ የሆነበትን ምክንያት ቀድሞ ያስረዳል ።
በዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ በሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ዘንድ አትሌቲክስን በመጠቀም ትስስርን ለመፍጠር ያለመ Run in the USA የተሰኘ የ5ኪሜ የሩጫ ውድድር ተካሄዷል። በሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያዊያን የስፖርት ፌዴሬሽን ዓመታዊ ፌስቲቫል መዝጊያ ቀን በነበረው ውድድር ታዳጊ ህጻናትም የ1 ማይል ውድድር አድርገዋል። ስለ ውድድሩ ፋይዳ ለማወቅ ሀብታሙ ስዩም ከውድድሩ አዘጋጆች መካከል አንዱ ከሆነው ኤርሚያስ አየለ ጋር አጭር ቆይታ አድርጓል ።
ባሳለፍነው ቅዳሜ ምሽት ሜሪላንድ ግዛት ውስጥ በሚገኘው ሞንት ጎመሪ ኮሌጅ የኪነጥበባት አዳራሽ ውስጥ ፣ በዮሃንስ ፈለቀ የተዘጋጀው «ዘ ኢንስ አንድ አውትስ» የተሰኘ ዘጋቢ ፊልም ተመርቋል። አንድ ኢትዮጵያዊ ፊልም ባለሙያ በስደት በሚኖርባት ዩናይትድ ስቴትስ ህልሙን ለማሳካት የሚያልፍበትን ውጣ ውረድ የሚያስቃኘው ፊልም ፣ ለእይታ በቀረበበት ምሽት ታዋቂ ገጣሚያንን ጨምሮ ዕውቅ ኢትዮጵያዊያን ስራቸውን ለታዳሚው አቅርበዋል።
በቅርቡ በተደረገው በሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያዊያን የስፖርት ፌዴሬሽን ፌስቲቫል ላይ ከተገኙ የክብር እንግዶች መካከል አንዱ ፣ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድንን ለታሪካዊ ድል እያበቁ የሚገኙት ዋና አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ናቸው ። አሰልጣኝ ውበቱ በተለይ ትውልደ-ኢትዮጵያዊያን የኢትዮጵያን እግር ኳስ በማሳደግ ረገድ ሊጫወቱት የሚችሉትን ሚና አስመልክተው ሀሳባቸውን ለቪኦኤ አካፍለዋል። ታዳጊዎች ህልማቸውን ለማሳካት ምን ማድርግ እንዳለባቸውም ሙያዊ ምክራቸውን ለግሰዋል።
ትውልደ- ኢትዮጵያዊያን ደንበኞች እና የንግድ ቤቶች ከሚፈተኑባቸው ጉዳዮች መካከል አንዱ በሀገርኛ ቋንቋ የሚያስተሳስራቸው አውታር ማነስ ነው። ይሄን የተመለከተ የወጣቶች ድርጅት ከ1000 በላይ የንግድ ድርጅቶች፣ አገልግሎት ሰጪዎች ፣ የዜና አውታሮች ፣የኃይማኖት ተቋማት እና ሌሎች ትውልደ-ኢትዮጵያዊያን ላይ አተኩረው የሚንቀሳቀሱ ድርጅቶችን አድራሻ ጠቋሚ እና አገናኝ መተግበሪይ ይፋ አድርጓል።
"ፊደል ኢ-ቡክ"፣ ህጻናትን ፊደል የሚያስቆጥር ፣ተረት የሚያወራ እና መዝሙር የሚዘምር የኤሌክትሪክ መጽሃፍ ነው ። የ5 ትውልደ-ኢትዮጵያዊያን የፈጠራ ስራ የሆነው የአማርኛ ንባብ መሳሪያ ፣ በተለይ በውጭ ሀገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ልጆቻቸውን በቀላሉ ንባብ ለማስተማር ያላቸውን ፍላጎት ለማገዝ የተሰራ እንደሆነ ተነግሯል። ሀብታሙ ስዩም ከመስራቾቹ መካከል አንዱ የሆነውን ጥላሁን ዓለሙን በመከናወን ላይ ባለው 39ኛው በሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያዊያን ስፖርት ፌዴሬሽን ፌስቲቫል ላይ አግኝቶ አነጋግሮታል ።
“ሀስኪ” ዮሃንስ ሓይሌ እና ሆሄያት ብርሃኑ የተባሉ ወጣት የሜካኒካል ምህንድስና ባለሙያዎች ያቋቋሙት ቴክኖሎጂ ድርጅት ነው። የቡና ገለባን ወደ አማራጭ ኃይል የሚለወጥ ሰርተው በማቅረባቸው የዚህ ዓመት የቴታል ስታርት አፐር የፈጠራ ውድድር አሸናፊ ሆነዋል። በተለያዩ በየመንግስት እና የግል ተቋማት መድረኮች ላይም ለስራቸው ዕውቅና እና ሽልማት አግኝተዋል። ስለ እንቅስቃሴያቸው የበለጠ እንሰማለን። ስለ "ሀስኪ" አጀማመር ዮሃንስ ቀድሞ ይነግረናል ።
39ኛው የኢትዮጵያዊያን የስፖርት ፌዴሬሽን በሰሜን አሜሪካ ፌስቲቫል እሁድ ሰኔ 26/2014 በሜሪላንድ ግዛት፣ በሜሪላንድ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ተጀምሯል ።ሀብታሙ ስዩም አከፋፈቱን ስነስርዓት ዐበይት ሁነቶች እንዲሁም የተሳታፊዎችን ሀሳብ ያካተተበትን ዘገባ በመቀጠል ያሰማናል ።
ኢትዮጵያ ውስጥ ህጻናትን የመንከባከብ አገልግሎትን ለማዘመን ያለመ ተቋም ስራ ከጀመረ መንፈቅ አልፎታል። መጠሪያ ስሙ "ሞግዚት" ሲሆን በቴክኖሎጂ ድልድይነት ወላጆች እና የሞግዚትነት አገልግሎት የሚሰጡ ባለሙያዎችን እያገናኘ ይገኛል። ሀብታሙ ስዩም ከተቋሙ መስራች እና ኃላፊ ሳምራዊት ታረቀኝ ጋር አጭር ቆይታ አድርጓል።
ቁጥራቸው በበዛ የራዲዮ እና የቴሌቭዥን ድራማዎች ደራሲነቱ እና አዘጋጅነቱ የሚታወቀው ሰለሞን ዓለሙ በተወለደ በ62 ዓመቱ በዛሬው ዕለት ከዚህ ዓለም ተለይቷል። /ሀብታሙ ስዩም የዕውቁን ከያኒ የቅርብ ጓደኞች እና የስራ አጋሮች ጠይቆ ያሰናዳውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ያዳምጡ/
ኢትዮጵያ በብዛት ስደተኞችን ከአስተናገዱ የአፍሪካ ሀገራት ሶስተኛ ደረጃ ላይ የምትገኝ ሀገር ናት።ሀገሪቱ በቅርብ ጊዜያት በርስበርስ ጦርነት ምክንያት ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባታል። ።የጦርነቱ ጉዳት በዜጎቿ ላይ ብቻ ሳይሆን የተሻለ ህይወት ፈልገው በግዛቷ ለተጠለሉት ስደተኞችም መትረፉን የተለያዩ ሪፖርቶች ያሳያሉ ። የዓለም ስደተኞች ቀን በሚከበርበት ዕለት ኢትዮጵያ የስደተኞችን ደህንነት ለማስጠበቅ ምን እየሰራች ነው ስንል ጠይቀናል?
ተጨማሪ ይጫኑ