መኖሪቸውን በሰሜን አሜሪካ ቨርጂኒያ ግዛት ያደረጉት ሁሴን አህመድ በታክሲ ሹፍርና ስራ ይተዳደራሉ፡፡ ከሥራ በተረፈ ሰዓታቸው፣ "ፈርስት ሂጂራ ፋውንዴሽን" በተሰኘው ግብረ ሰናይ ተቋም ውስጥ የማኅበረሰብ ሥራ ይከውናሉ፡፡ የኢድ አልፈጥርን በዓል ምክንያት አድርገው፣ ስደት እና በዓልን የተመለከቱ ወጎችን ያካፍሉናል፡፡
በዩናይትድ ስትቴትስ፣ በዋሽንግተን ዲሲ ከተማ እና አካባቢዋ የሚኖሩ በርካታ ኢትዮጵያዊያን እና ትውልደ - ኢትዮጵያዊያን የእስልምና ዕምነት ተከታዮች የኢድ አልፈጥር በዓልን ሰብሰብ ብለው አክብረዋል፡፡ ፈርስት ሂጅራ ፋውንዴሽን ያስተባበረው የዘንድሮ ልዩ አከባበር የተከናወነው ሮክ ክሪክ በተሰኘ መናፈሻ ውስጥ ነው፡፡
በዩናይትድ ስትቴትስ፣ በዋሽንግተን ዲሲ ከተማ እና አካባቢዋ የሚኖሩ በርካታ ኢትዮጵያዊያን እና ትውልደ- ኢትዮጵያዊያን የእስልምና ዕምነት ተከታዮች የኢድ አልፈጥር በዓልን ሰብሰብ ብለው አክብረዋል፡፡ ፈርስት ሂጅራ ፋውንዴሽን ያስተባበረው የዘንድሮ ልዩ አከባበር የተከናወነው ሮክ ክሪክ በተሰኘ መናፈሻ ውስጥ ነው፡፡ በዮናይትድ ስቴትስ የኢትዮጵያ አምባሳደር በክብር እንግድነት በተገኙበት በዚህ አከባበር ላይ ሰላም፣ አንድነት እና ልግስና ሲሰበክ ተሰምቷል፡፡
አባል ሀገራት የሰብአዊ እና ዲሞክራሲያዊ መብቶችን ለማስከበር ያደረጉት ጥረት የሚመለከተው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ መብት ምክር ቤት ግምገማ ከሰሞኑ ተካሄዷል፡
ትናንት “ገበታ ለሸገር” በሚል የተሰየመ ፣ገቢው አዲስ አበባን ለማስዋብ የሚውል የእራት ዝግጅት በአጤ ምኒሊክ እልፍኝ ውስጥ ተከናውኗል፡
ዓለም አቀፉ የግዛት ውስጥ መፈናቀል ተቆጣጣሪ ማዕከል በምኅጻሩ IDMC ከሰሞኑ ባወጣው ሪፖርት እስከ አውሮጳዊያኑ ታህሳስ 31 /2018 ባለው ጊዜ በተደረገ ቆጠራ ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ ወደ 3 ሚሊየን የሚጠጉ ዜጎች በግጭቶች ምክንያት ከቀያቸው እንደተፈናቀሉ ይፋ አድርጓል፡፡
ከተለምዶ ወጣ ባለ መልኩ በመጠሪያ ስማቸው ላይ የእናታቸውን ስም የሚያካትቱ ኢትዮጵያዊያን እየተበራከቱ ነው፡፡ ከዚህ ዑደት ፊታውራሪዎች መካከል የኪነ-ጥበብ ሰዎች ይገኙበታል፡፡
እሸቱ መለሰ -ከጎሳ ፖለቲካ እስከ ማህበራዊ ጉዳዮች፣ከጾታዊ ጽንሰ- ሀሳቦች እስከ ሰብአዊ መብት ሙግቶች ፤ በሚዳስሱ አስቂኝ ስራዎቹ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ትኩረትን ያገኘ ወጣት ከያኒ ነው፡፡
የመናገር ነጻነትን ጨምሮ ስለ በርካታ ዲሞክራሲያዊና ሰብአዊ መብት ጽንሰ-ሀሳቦች ለዓለም ካስተማሩ ፈላስፎች መካከል አንዱ የሆነውን፣የሶቅራጠስ ታሪክ የሚዘክር ቲያትር በበብሄራዊ ቲያትር በመታየት ላይ ይገኛል፡፡
የመናገር ነፃነት የሚዘከርበት ውይይት እና ትርዒት ዛሬ ይደረጋል፡፡
ባለፈው ሳምንት መገባደጃ ላይ በአርሲ ዩኒቨርሰቲ በተግባር ልምምድ ላይ የሚገኙ የህክምና ተማሪዎች ያነሱትን ተቃውሞ በተመለከተ አንድ ዘገባ ማስደመጣችን ይታወሳል፡፡
በሳምንቱ መገባደጃ ላይ የስነ-ልቦና እና የኢኮኖሚ ጫና ፈጥሮብናል ያሉትን አሰራር የተቃወሙ በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ያሉ በተግባር ልምምድ ላይ የሚገኙ የህክምና ተማሪዎች ቅሬታቸውን በተለያዩ መንገዶች ሲገልጹ ታይተዋል፡፡
በስልኮች ላይ የሚጫኑ መተግበሪያዎች ወይንም Applications የሰዎችን ህይወት በእጅጉ የሚያግዙ መላዎች ናቸው፡፡ ሰዎች ከዓመታት በፊት በልፋት የሚያገኟቸውን መረጃዎች እና አገልግሎቶች ዛሬ ባሉበት በስልካቸው ሰሌዳ ላይ ያገኛሉ፡፡
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ንብረት የሆነውና ቢሾፍቱ አቅራቢያ የወደቀው በበረራ ቁጥር ኢቲ 302 ቦይንግ 737 ማክስ ኤይት አይሮፕላን አደጋ ተጎጂዎች የካሳ ጥያቄ በየትኛው ሕግ ይዳኛል?
ከቻይና ብድር በመውሰድ ከአፍሪካ በሁለተኛ ደረጃ ላይ መሆኗ የሚነገርላት ኢትዮጵያ ፣ ከሰሞኑ የብድር አከፋፈልን የተመለከተ ውይይት ከአበዳሪዎ ቻይና ጋር መጀመሯ ተሰምቷል፡፡ለመሆኑ ኢትዮጵያ ከቻይና የወሰደችውን ዕዳ መክፈል የማትችልበት አቅም የላትምን ?(ዘገባው ይዳስሰዋል)
በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በአሰቃቂ ሁኔታ በተገደሉ ማግስት የቀድሞ መንግስት ከፍተኛ ባለስልጣን እና የዓለም አቀፉ የምግብ ፕሮግራም ባልደረባ የነበሩት ሻ/ቃ ዳዊት ወ/ጊዮርጊስ ወደ ርዋንዳ -ኪጋሊ ተላኩ፡፡‹‹በሰው ልጅ ጭንቅላት ሊዳሰስ፣ሊታወቅ (ሊገመት) ›› የማይችል ሲሉ የሚገልጹትን ግፍ በዐይናቸው ለማየት ቻሉ፡፡