የአሜሪካን ኢትዮጵያን የሚመለከት ወቅታዊ አቋም ያወገዘ ሰልፍ ተደረገ
Your browser doesn’t support HTML5
የዮናይትድ ስቴትስ መንግስት በኢትዮጵያ የትግራይ ክልል ውስጥ ተከስቷል ያለውን አሳሳቢ የሰብዓዊ መብቶች እና ሰብዓዊ አገልግሎቶች ሁኔታ ጠቅሶ፣ የያዘው ወቅታዊ አቋም ትክክለኛ ባልሆኑ መረጃዎች ላይ የተመረኮዘ መሆኑን የገለጹ ትውልደ -ኢትዮጵያዊያን እና ኤርትራዊያን ትናንት በዋሺንግተን ዲሲ ሰላማዊ ሰልፍ አድርገዋል።