ትኩረቱን በህግ የበላይነት መከበር ላይ ያደረገው የዓለም-ፍትህ መርሃ-ግብር ‘ወርልድ ጀስቲስ ፕሮጀክት’ የተሰኘ ተቋም ህግን በማስከበር እና የህግ የበላይነትን በማክበር ረገድ ሀገራት ያላቸውን ደረጃ ይፋ በማድረግ ይታወቃል፡፡
ዝቀተኛ ደረጃን ካገኙ 10 ሀገራት መካከል ኢትዮጵያን ጠቅሷል፡፡
ዋሽንግተን ዲሲ —
እንዲህ በእየአደባባዩ ሳይቀር በተገቢው የብቃት ደረጃ ላይ አለመገኘቱ የሚጠቀስበትን የፍትህ ስርዓት ለማሻሻል ርምጃዎች እየተወሰዱ ስለመሆኑ ከሰሞኑ በዋሺንግተን ከተማ በተደረገ የማስገንዘቢያ መድረክ ላይ ተወስቷል፡፡
የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚደንት ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ በውጭ ሀገራት ከሚገኙ የህግ ባለሙያዎችና ሙሁራን ጋር በመከሩበት በዚህ መድረክ ላይ የኢትዮጵያን የፍትህ ስርዓት የፈተኑ ችግሮች ፣ወደ መፍትሄ አድራሽ ሀሳቦች፣ እንዲሁም የዘመነ ስርዓት አላቸው የሚባሉ ሀገራት ልምዶች ተጋርተዋል፡፡
ሀብታሙ ስዩም የውይይቱን አንኳር ሀሳቦች በቀጣዩ ዘገባው ያስቃኘናል፡፡
Your browser doesn’t support HTML5
ትውልደ-ኢትዮጵያዊያን እና የኢትዮጵያ ፍትህ ስርዓት ማሻሻያ ውጥን