ዋሽንግተን ዲሲ —
በሰሜን አሜሪካ የሚገኙ ከኢትዮጵያ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ጋር ግንኙነት ያላቸው ማህበራት የፊታችን ሀሙስ መስከረም 8/2012፣ በአራት የዩናይትድ ስቴትስ እና ካናዳ ከተሞች ይካሄዳሉ የተባሉ ሰላማዊ ሰልፎችን ጠርተዋል፡፡
የሰልፉን ዓላማ እና ግብ ለማብራራት በጠሩት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይም ፣ ‹‹በቤተክርስቲያን እና ምዕመናን ላይ እያየለ በመጣው ጥቃት ተቆጥተናል፣ መንግስት ጥቃት ፈጻሚዎችን ለፍርድ ማቅረብ አለበት!›› ሲሉ አሳስበዋል፡፡
ሀብታሙ ስዩም በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ ተገኝቶ ነበር፡፡ተከታዩን ዘገባ አጠናቅሯል፡
Your browser doesn’t support HTML5
በሰሜን አሜሪካ ከኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ጋር ግንኙነት ያላቸው ማህበራት ሰልፎችን ጠርተዋል