ቆይታ ከሰብአዊ ድጋፍ አሰባሳቢው ሙሉ ኃይለስላሴ ጋር
Your browser doesn’t support HTML5
ከሶስት ሚሊዮን ብር በላይ ገንዘብ ከለጋሾች በማሰባሰብ የኮሮና ቫይረስን ስርጭት ለመቆጣጠር በሚደረገው እንቅስቃሴ ምክንያት ለኢኮኖሚያዊ ችግር ለተዳረጉ ሰዎች እርዳታ እየሰጠ ያለ አንድ ወጣት እናስተዋውቃችሁ::
ሙሉ ኃይለስላሴ ይባላል። በትግራይ ክልል መቐለ ከተማ ነዋሪ ነው:: እስከ አሁን ካሰባሰበው ገንዘብ ከሁለት ሚልዮን ብር በላይ የሚሆነውን ወጪ በማድረግ ለተቸገሩ ወገኖች የምግብ እርዳታ እንደተደረገ ለአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ ተናግሯል።::