Me too ፣‹‹እኔም !›› በሚል የሚጠራው የጸረ-ጾታ ጥቃት ዘመቻ በምዕራቡ ዓለም ስልጣናቸውን ፣ሀብታቸውን እና ዝናቸውን መከታ በማድረግ የወሲብ ጥቃቶችን ያደረሱ ሰዎችን በማጋለጥ ይታወቃል፡፡
ዋሽንግተን ዲሲ —
ይሄንን መብትን የማስከበር ሂደት በምሳሌነት የወሰዱ ወጣቶች ፣ኢትዮጵያዊያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ላይ የሚደርሱ ወሲባዊ ጥቃቶችን የሚያጋልጥ Me too Ethiopia የተሰኘ የበይነ መረብ መርሃ-ግብር ጀምረዋል፡፡
በይነ-መረቡ ይፋ በተደረገ በጥቂት ጊዜ ውስጥ በርከት ያሉ በሴቶች እና ወንድ ህጻናት ላይ የደረሱ ጥቃቶችን የሚያጋልጡ ታሪኮች እንደተጋሩበት ከመስራቾች መካከል አንዷ የሆነችው ትዕምርት ሽመልስ ለሀብታሙ ስዩም ነግራዋለች፡፡
ሙሉ ቆይታውን ያዳምጡ፡፡