የመጤ ባዕዳን ላይ በተመሠሰረተ ጥላቻ ስድስት ኢትዮጵያውያን ሞተዋል

ዘነፎብያ (Xenophobia) ወይም በመጤ ባዕዳን ላይ የተመሠሰረተ ጥላቻ

በደቡብ አፍሪቃ ደርበን ከተማ ዘነፎብያ (Xenophobia) ወይም በመጤ ባዕዳን ላይ በተመሠሰረተ ጥላቻ ምክንያት ስድስት ኢትዮጵያውያን ላይ የደረሰውን ጥቃት የዐይን ምስክሮች ይገልጻሉ።

ቀደም ሲል በዜናችን ላይ እንደተገለጸው፣ በደቡብ አፍሪቃዋ ደርበን፣ ዘነፎብያ (Xenophobia) በተሰኘ በመጤ ባዕዳን ላይ በተመሠሰረተ ጥላቻ፣ ስድስት ኢትዮጵያውያን ላይ አሰቃቂ ግድያ ተፈጽሞባቸዋል።

ዜናውን እዚያው ከደርባን ለአሜሪካ ድምፅ ያደረሱን የዐይን ምስክሮች እንደገለጹት፣ ኢትዮጵያውያኑ ላይ የሚፈጸመው ዝርፊያና ድብደባ ሳያንስ፣ ቤንዚን ሰውነታቸው ላይ አርከፍክፎ እስከ ማቃጠል ተደሯል።

አዲሱ አበበ ሁለት ደርባን ኗሪ ኢትዮጵያውያንን አነጋግሮ ተለከታዩን አእርቧል። የድምጽ ፋይሉን በመጫን ያዳምጡ።

Your browser doesn’t support HTML5

በመጤ ባዕዳን ላይ በተመሠሰረተ ጥላቻ ስድስት ኢትዮጵያውያን ሞተዋል