በምዕራብ ጎንደር ዞን፣ ባለፈው ሳምንት እሑድ ታጣቂዎች በከፈቱት ተኩስ፣ አንዲት ሱዳናዊት ስደተኛን ጨምሮ ሁለት ኢትዮጵያውያን መገደላቸውን፣ የመተማ ወረዳ አስተዳደር አስታወቀ፡፡
Your browser doesn’t support HTML5
በመተማ ወረዳ አንዲት ሱዳናዊትን ጨምሮ ሦስት ሰዎች በታጣቂዎች ተገደሉ
የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ ደሳለኝ ሞገስ ግድያው የተፈጸመው፣ ከምዕራብ ጎንደር ዞን ዋና ከተማ ገንደ ውኃ ወደ ነጋዴ ባሕር ሲጓዝ በነበረ አነስተኛ የሕዝብ ማመላለሻ መኪና ላይ በተከፈተ ተኩስ እንደኾነ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል፡፡
የግድያ ድርጊቱን፣ የኢትዮጵያ የስደተኞች እና ከስደት ተመላሾች አገልግሎትም አረጋግጧል፡፡