በዲሞክራቲክ ኮንጎ ግጭቱ ተባብሶ ቀጥሏል

Your browser doesn’t support HTML5

በሩዋንዳ የሚደገፉት ኤም 23 ተብለው የሚታወቁት የአማጺ ቡድኖች የዴሞክራቲክ ኮንጎ ቁልፍ ከተማ የሆነችውን ምሥራቃዊ ጎማን ትላንት ሰኞ ሙሉ ለሙሉ መቆጣጠራቸውን ተከትሎ፤ በዴሞክራቲክ ኮንጎ አለመረጋጋት እና ሁከት ሰፍኗል። በዋና ከተማዋ ኪንሻሳ ተቃዋሚዎች በሩዋንዳ፣ ፈረንሳይ፣ ዩናይትድ ስቴትስ እና ኬኒያ ኤምባሲዎች ላይ ጥቃት ፈጽመዋል።

ጎማ ውስጥም ዝርፊያ፣ አስገድዶ መድፈርን ጨምሮ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሰዎች በመሣሪያ ጉዳት ደርሶባቸው በሆስፒታሎች እንደሚገኙ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አስታውቋል።

የመንግሥታቱ ድርጅት በዴሞክራቲክ ኮንጎ አስቸኳይ የተኩስ አቁም እንዲደረግ እና ወደ ውይይት እንዲገባም ጥሪ አቅርቧል።