የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ኢትዮጵያ ናቸው

Your browser doesn’t support HTML5

የዩናይትድ ስቴትስ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ ልዑክ አምባሳደር ጄፍሪ ፌልትማን አዲስ አበባ ገብተዋል። ፌልትማን ከሀገሪቱ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ጋር ተገናኝተው እንደሚወያዩ የተገለጸ ሲሆን ትናንትም ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ተቀብለው ያነጋገሯቸው መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።