ጃክ መቶ ዓመቱን ደፈነ

ግንቦት 21 / 1909 ዓ.ም በዩናይትድ ስቴትስ ምሥራቃዊ ግዛት አንድ "ጃክ" እያሉ የሚጠሩት ኮከብ ተወለደ፡፡ በነፍስ ገዳይ ጥይት በ46 ዓመት ዕድሜው እስከተቀጨ ድረስም በዚህች ምድር ላይ ኖሮ እነሆ እስከዛሬ በዓለሙ ሁሉ እያስተጋባ የሚዘከር፣ የሚነገር ስም ሆነ - ጃን ፊትዠራልድ ኬኔዲ፡፡

ግንቦት 21 / 1909 ዓ.ም በዩናይትድ ስቴትስ ምሥራቃዊ ግዛት አንድ "ጃክ" እያሉ የሚጠሩት ኮከብ ተወለደ፡፡ በነፍስ ገዳይ ጥይት በ46 ዓመት ዕድሜው እስከተቀጨ ድረስም በዚህች ምድር ላይ ኖሮ እነሆ እስከዛሬ በዓለሙ ሁሉ እያስተጋባ የሚዘከር፣ የሚነገር ስም ሆነ - ጃን ፊትዠራልድ ኬኔዲ፡፡

Your browser doesn’t support HTML5

ጃክ መቶ ዓመቱን ደፈነ

የዩናይትድ ስቴትስ ሰላሣ አምስተኛ ፕሬዚዳንት ሊሆን የተወለደው ጃን ኤፍ ኬኔዲ በማሳቹሴትሷ ብሩክሊን ልክ የዛሬ መቶ ዓመት ዛሬ፤ የዚህችን ምድር አየር ለመተንፈስ በእንግድነት የመጣ ጊዜ ሲያልፍ አካሉ የምታርፍባት ቁራሽ ምድር በዓለም ከታወቁ የቱሪስት መስኅቦች አንዷ ትሆን ዘንድ የጠረጠረ ማንም አልነበረም፡፡ ከዋሺንግተን ዲሲ ወጣ ብሎ አርሊንግተን መካነ-እረፍት ይገኛል፤ በዚያም ጃክ ተኝቷል፡፡ ብዙና ብዙ ሰው ላይቀሰቅሰው እምብዛም ሳይጨነቅ ሰላም ሊለው ይተራመሳል፡፡

ጃን ኤፍ ኬኔዲ ተመትተው የወደቁ ጉዜ ገና ያልተወለዱ፤ አብረዋቸው የነበሩ ወይም ማንነታቸውን በአካል የሚያውቁ፤ ሁሉም ወደ አርሊንግተን በየቀኑ ይጎርፋሉ፡፡

ፎቶ ፋይል

ኬኔዲ (ጃክ) በ43 ዓመት ዕድሜአቸው በ1953 ዓ.ም ቃለ-መሃላ ፈፅመው ዋይት ሃውስ ገቡ፡፡ በዚያች ዕለት ያሰሙት ንግግርና ያስተላለፉት ቁልፍ መልዕክት ለጃን ኤፍ ኬኔዲ ሲጠቀሱላቸው ይናራሉ፡፡ «እንኪያስ ሃገሬ ምን ታደርግልኛለች? አትበሉ፤ ይልቅ እኔ ለሃገሬ ምን ላደርግላት እችላለሁ በሉ እንጂ!»

የፖለቲካ ፓርቲዎችም ለጋራ ግቦች እንዲሠሩ አዲሱ ፕሬዚዳንት ግብዣና ጥሪ አስተላለፉ፡፡

"ዛሬ የምናከብረው የፓርቲ ድል አይደለም፤ ይልቅ አንድን ፍፃሜ፣ ደግሞም አንድን ጅምር የሚያበስር፤ መታደስን፣ ደግሞም ለውጥን የሚያውጅ የነፃነት ፈንጠዝያ እንጂ!"

ኬኔዲ ፒስ ኮር እየተባለ የሚጠራውን የሰላም ጓዶች የበጎ ፍቃደኞች ዓለምአቀፍ ተልዕኮ መሠረቱ፤ ጥቁር ወጣቶች ምርጫቸው በሆነና በፈለጉበት ዩኒቨርሲቲ መማር እንዲችሉ የሚደነግግ ሕግ አወጡ፡፡ የአሜሪካ ቀልብ ወደ ጨረቃ መጓዝ ላይ እንዲያርፍ አደረጉ፡፡

ኬኔዲ አርባ አራተኛው ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማን ጨምሮ ለብዙ ወጣት አሜሪካዊያን፣ ተከታታይ የፖለቲካ ትውልዶች አርአያና ፋና ሆነዋል፡፡

የተያያዘውን ቪድዮና የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

Your browser doesn’t support HTML5

ጃክ መቶ ዓመቱን ደፈነ