የዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት አባላትና ሴናተሮች የኢትዮጵያ መንግሥት ዓለም አቀፍ የሕጻናትን ጉዲፈቻ እንዲቆም የሚያስገድደውን ውሳኔ በድጋሚ እንዲያጤነውና በሕጋዊ መንገድ የጉዲፈቻ አሠራር ጀምረው በሂደት ላይ ያሉ ቤተሰቦች ጉዳያቸውን እንዲጨርሱ እንዲደረግ ለኢትዮጵያ መንግስት ደብዳቤ ጻፉ።
ዋሽንግተን ዲሲ —
የምክር ቤቱ አባላትና ሴናተሮቹ በጻፉት ደብዳቤ፤ «ኢትዮጵያ በጉዲፈቻ ጉዳይ ላይ ወደፊት የምትከተለውን ፖሊሲ አስመልክቶ መንግሥትዎ የወሰደውን ውሣኔ እያከበርን ቀደም ሲል ተጀምረው እስከ ሚያዝያ 13/2009 ዓ.ም እንቅስቃሴ ላይ ለነበሩ ጉዳዮች የሚሰጠው መፍትኄ እንዲፋጠን ለማድረግ እገዛዎን እንዲያደርጉልን እንጠይቃለን፡፡ እነዚህ ሕፃናት ከአሳዳጊ ቤተሰቦቻቸው ጋር እንዲገናኙ በመርዳት በኩል ከእኛ ጋር ያለመተባበር በሁለቱ ሀገሮቻችን መካከል ያለውን ግንኙነት እንዳይጎዳው እንሠጋለን፡፡» ብለዋል።
የኢትዮጵያ መንግሥት በጉዳዩ ላይ የሚሰጠውን ምላሽ ይዘን እንመለሳለን።
Your browser doesn’t support HTML5
74 የምክር ቤት አባላትና 47 ሴናተሮች ለጠ/ሚ ኃይለማርያም ደሳለኝ ደብዳቤ ፃፉ