ከትግራይ ዩኒቨርሲቲዎች ያቋረጡ ተማሪዎች እሮሮ አሰሙ

Your browser doesn’t support HTML5

ከትግራይ ዩኒቨርሲቲዎች ያቋረጡ ተማሪዎች እሮሮ አሰሙ

በትግራይ ክልል ካሉ ዩኒቨርሲቲዎች እና ከወልዲያ ዩኒቨርሲቲ በአማራ ክልል ወዳሉ ሦስት ዩኒቨርሲቲዎች የተመደቡ ተማሪዎች እስካሁን መፍትሔ አላገኘንም አሉ።

ተማሪዎቹ ቅሬታቸውን ለማሰማት ወደ ትምህርት ሚኒስቴር በተደጋጋሚ ቢያመሩም መልስ የሚሰጣቸውን አካል እንዳላገኙ ተናግረዋል፡፡

ተማሪዎቹ አሁን ላይ ለስነልቦና እና ለሌሎች ችግሮች መጋለጣቸውንም ለአሜሪካ ድምፅ ገልጸዋል፡፡ ከሚኒስቴሩ ምላሽ ለማግኘት የተደረገው ጥረት ለጊዜው አልተሳካም፡፡