የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ እርዳታ ማስተባበሪያ ቢሮ ባወጣው መግለጫ ገንዘቡ ቀደም ሲል ከተገመተው በላይ መጨመሩን አስታውቋል።
አዲስ አበባ —
በድርቅ የተጎዱ ኢትዮጵያውያንን ለመርዳት የሚያስፈልገው ገንዘብ መጠን ቀደም ሲል ከተገመተው በላይ መጨመሩን፥ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ እርዳታ ማስተባበሪያ ቢሮ አስታውቋል።
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሓፊ ባን ኪ ሙን በኢትዮጵያ የተከሰተውን ድርቅና የምግብ እጥረት ሁናቴ በቅርብ ለመከታተል ወደ ኢትዮጵያ በተጓዙበት ወቅት የተነሳ ፎቶ
በዚህም መሠረት፥ የሚያስፈልገው ገንዘብ ከአንድ ነጥብ አራት ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ወደ አንድ ነጥብ አምስት ቢሊዮን ከፍ ማለቱን ይፋ አድርጓል።
እስክንድር ፍሬው የላከውን ዝርዝር ከድምጽ ፋይሉ ያድምጡ።
Your browser doesn’t support HTML5
በድርቅ የተጎዱ ኢትዮጵያውያንን ለመርዳት የሚያስፈልገው ገንዘብ ከ1.4 ቢሊዮን ወደ 1.5 ቢሊዮን ዶላር ከፍ ማለቱን የተ.መ.ድ.ይፋ አደረገ