ጎ-ፈንድ-ሚ ወይም (GoFundMe) በግርዱ ወደ አማርኛ ሲመለስ፤ “ድጋፍህን ስጠኝ፤” በሚል ስያሜ በሚታወቀውና በሚልዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች ከ1 ቢልዮን ዶላር በላይ በ 365 ቀናት ውስጥ ሊሰበስቡ የሚችሉበት ድረ-ገጽ ነው።
ሁለት ኢትዮጵያውያን፣ ዶ/ር አበበ ሃረገውይንና አብርሃም ተፈሪ ድረ-ገጹን በመጠቀም በአሁኑ ጊዜ ኢትዮጵያ ውስጥ የምግብ እጥረት ለደረሰባቸው ወገኖች እርዳታ አሰባስበዋል። እስከ ዛሬ ከ30,000 ዶላር በላይ የሰበሰቡ ሲሆን፣ በዛሬው እለት ገንዘቡን ለዓለም ምግብ ፕሮግራም (WFP) ለተራቡ ወገኖች እንዲያደርስ አስረክበዋል።
ሳሌም ሰለሞን በርክክቡ ላይ ተገኝታ ያጠናቀረችውን ቃለ-ምልልስ ከዚህ በታች ካለው የድምጽ ፋይል ያዳምጡ።
Your browser doesn’t support HTML5
ሁለት ኢትዮጵያውያን ከ30,000 ዶላር በላይ ለዓለም ምግብ ፕሮግራም አስረከቡ
በተጨማሪም የቪድዮ ፋይሉን በመጫን የኢትዮጵያኑን መልእክት ይመልከቱ።
Your browser doesn’t support HTML5
ሁለት በዳያስፖራ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ከ30,000 ዶላር በላይ ለዓለም ምግብ ፕሮግራም አስረከቡ
የፎቶ መድብሎቻችንንም ከዚህ በታች ካለው ፋይል ይመልከቱ።
ሁለት ኢትዮጵያውያን ከ30,000 ዶላር በላይ ለዓለም ምግብ ፕሮግራም አስረከቡ