የትረምፕ የበዓለ ሲመት ንግግር እና የበዓል ትርዒቶች

  • ቪኦኤ ዜና

Your browser doesn’t support HTML5

የትረምፕ የበዓለ ሲመት ንግግር እና የበዓል ትርዒቶች

ዶናልድ ትረምፕ ትላንት ሰኞ ቃለ መሐላቸውን ፈጽመው 47ኛ ፕሬዝደንት ሆነዋል። ከቃለ መሐላቸው በኋላ በዋሽንግተን ዲሲ ካፒታል አሬና በተባለው የስፖርት እና የመዝናኛ ስታዲየም በተካሂደ የበዓለ ሲመት በዓል ላይ ተገኝተዋል።

አዲሱ ፕሬዝደንት እንደ አውሮፓውያን የዘመን አ2021 ጥር ስድስት በዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት የምርጫውን ውጤት ማረጋገጫ ሂደት ለማደናቀፍ ካደረጉት ሙከራ በተያያዘ ለተፈረደባቸው ደጋፊዎቻቸው ምህረት የሚሰጥ አስፈጻሚ ትዕዛዝ እንደሚፈርሙ ለታዳሚው አስታውቀው ነበር።