ባለፉት 28 ዓመታት ለደቡብ ክልል ከሲዳማ ውጭ የሌላ ብሄር ተወላጅ በርዕሰ-መስተዳደርነት ሲሾም አቶ ርስቱ ይርዳው ከአቶ ኃይለማርያም ቀጥሎ ሁለተኛ ሰው ሆነዋል።
ሀዋሳ —
ሌላ ምርጫ እስካልተካሄደ ክልሉን የሚመራው የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ /ደኢህዴን/ በመሆኑ አዲስ ነገር አይፈጠርም ሲሉ የፖሊቲካ ሣይንስና የዓለም አቀፍ ግንኙነት ምሁር አቶ ዳያሞ ዳሌ ለቪኦኤ ተናግረዋል።
ክልሉን በምክትል ርዕሰ መስተዳደርነት ለመምራት በህዝብ እንደራሴዎች ፊት ቃለ-መሃላ የፈፀሙት አቶ ርስቱ ይርዳው በክልሉ አስተማማኝ ሰላም ማረጋገጥና የህግ የበላይነት ማስከበርን ቀዳሚ ተግባራቸው እንደሚያደርጉ ተናግረዋል።
የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
Your browser doesn’t support HTML5
አዲሱ የደቡብ ፕሬዚዳንት
Your browser doesn’t support HTML5
የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መሰተዳደር ማን ናቸው?