የገዳ ስርዓት አንዱ አካል የሆነው የኦሮሞ ሴቶች "ስንቄ" ባህል የእርቅና የሰላም ተምሳሌት ነው፡፡
ሀዋሳ —
"ስንቄ" ሴቶች ነፃነታቸውና መብታቸውን የሚያስከብሩበትና ማኅበራዊ ኃላፊነት የሚሸከሙበት ባህላዊ ሥርዓት ነው ብሏል የኦሮሚያ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ፡፡
"ስንቄ" በጋዳ ስርዓት ሴቷን ከአባጋዳ ጋር አቻ የሚያደርጋት የ"Hadha"ስንቄ" ምልክት ነው ተብሏል፡፡
የሱዳን ሴቶች የባህልና የሰላም ሉዑካን ቡድን የ "ስንቄ" ባህል በአሮሚያ ክልል ምዕራብ አርሶ ዞን ኮፌሌ ከተማ ድረስ መጥተው ጎብኝተዋል፡፡
የልዑኩ መሪ ፕሮፌሰር ሜኪ ሀሻብሊ ኢትዮጵያ ግጭቶችን በባህላዊ መንገድ በመፍታት ረገድ ጥሩ ተሞክሮ አላት ብለዋል፡፡
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
Your browser doesn’t support HTML5
ስንቄ