የራዲዮ መፅሔት ልዩ ልዩ ቅንብሮች! የዓመቱ ቀጠሮ የሳምንቱ ወጎች፤

ከሰሜን አሜሪካው የኢትዮጵያውያን የስፖርት ፌዴሬሽን - ESFNA፤ የመላው ኢትዮጵያውያን ስፖርት ማኅበር - AESAONE እና ከጃኖ የሙዚቃ አባላት ጋር።

Your browser doesn’t support HTML5

የሳምንቱ ራዲዮ መጽሔት ቅምሻ ድምጾች፤ የዓመቱ ቀጠሮ የሳምንቱ ወጎች


Your browser doesn’t support HTML5

ቃለ ምልልስ ከሰሜን አሜሪካው የኢትዮጵያውያን የስፖርት ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ተሥፋዬና ከእውቁን የስፖርት ሰው አቶ ፍቅሩ ኪዳኔ ጋር፤


Your browser doesn’t support HTML5

ቃለ ምልልስ ከመላው ኢትዮጵያውያን የስፖርት ማኅበር ፕሬዝዳንት አቶ እያያ አረጋ ጋር፤


Your browser doesn’t support HTML5

ጃኖዎች በአሜሪካ


የሰሜን አሜሪካው የኢትዮጵያውያን የስፖርት ፌዴሬሽን ሰላሳኛ ዓመታዊ ክብረ በዓልና የሰላሳ ዓመታት ጉዞ ላይ ያተኮረ ውይይት፤ የፌዴሬሽኑን ጥንካሬ፥ ሥኬት ፈተናና ድክመቶቹን እንመረምራለን።

በማስከተልም ሁለተኛ ዓመቱን ያከበረውን የመላው ኢትዮጵያውያን ስፖርት ማኅበር የዘንድሮ አከባበርና የማኅበሩን አጠቃላይ ይዞታ እንቃኛለን።

ጃኖ የሙዚቃ ባንድ አባላት ከስቱዲያችን ይገኛሉ። ያዜማሉ እንወያያለን።

በጎረቤት ሜሪላንድ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ፓርክ ዓመታዊ በዓሉን ባከበረው የኢትዮጵያውያን የስፖርት ፌዴሬሽን ሰላሳኛ ዓመት ጉዞና በዘንድሮው ክንውኑ ዙሪያ ፕሬዝዳንቱን አቶ ጌታቸው ተሥፋዬንና እውቁን የስፖርት ሰው አቶ ፍቅሩ ኪዳኔን እንጠይቃለን።

የመላው ኢትዮጵያውያን የስፖርት ማኅበር የዘንድሮ አከባበር ምን መልክ ነበረው? መሠናዶውና ክንዋኔውሳ? ከማኅበሩ ፕሬዝዳንት አቶ እያያ አረጋ ጋር ቆይታ ይኖረናል።