አዲሱ የቀን ገቢ ግምት በነጋዴዎችና በግብር ሰብሳቢው መካከል የፈጠረው አለመግባባት አሁንም እንደቀጠለ ነው። የአሜሪካ ድምጽ ያነጋገራቸው ነጋዴዎች በተደረገው ግምት ላይ ተቃውሞና አቤቱታ እያቀረቡ ሲሆን በአቤቱታዎቹ ዙሪያ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት የኮሙዩንኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ አዲሱ አረጋን አነጋግረናቸዋል።
በአዲስ አበባ እና በኦሮሚያ ክልል የሚገኙ ነጋዴዎች በተደጋጋሚ ለዝግጅት ክፍላችን ሲናገሩ የቀን ገቢ ግምቱ በጣም የተጋነነ እንደሆነ በመግለጽ "ፍትሐዊ አይደለም" ብለውታል።
ጽዮን ግርማ የነጋዴዎቹ አቤቱታ ይዛ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት የኮሙዩንኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ አዲሱ አረጋን አነጋግራለች።
Your browser doesn’t support HTML5
በነጋዴዎች አቤቱታ ዙሪያ ከአቶ አዲሱ አረጋ ጋር የተደረገ ቃለምልልስ
አድማጮች የአዲስ አበባ ነጋዴዎችን በተመለከተ በኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉሙሩክ ባለሥልጣን የአዲስ አበባ የታክስ ፕሮግራም እና ልማት ሥራዎች ዘፍር ምክትል ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ነጻነት አበራ ለማግኘት ተደጋጋሚ ጥረት አድርገን እሳቸው ለጊዜው እንደሌሉ ተነግሮናል። ያናግሯችኋል የተባልነውን ተወካይም በዛሬው ዕለት ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም በነገው ዕለት ይዘን ለመመለስ ጥረት እናደርጋለን።