በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን ሆሮ ቡሉቅ ወረዳ እና በሰሜን ሸዋ ደራ ወረዳ ሰዎች መገደላቸው ተገለፀ
Your browser doesn’t support HTML5
በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን ሆሮ ቡሉቅ ወረዳ የመንግሥት ፀጥታ ኃይሎች የኦሮሞ ነፃነት ሸማቂዎችን ከመደገፍ ጋር በተያያዘ ሁለት ወጣቶችንና አንድ መምህር ገደሉ ሲሉ ከቤተሰብ መካከል የቅርብ ዘመድ ነኝ ያሉ ግለሰብ ገለፁ።
የወረዳው ፀጥታና አስተዳደር ፅህፈት ቤት ኃላፊ ግለሰቦቹ ስለመገደላቸው ለፅህፈት ቤታቸው ያሳወቀ ባለመኖሩ ምንም አይነት ምርመራ አለመደረጉን አስታውቋል።