በነአቶ በቀለ ገርባ ጉዳይ ጠበቃቸው እሮሮ አሰሙ

ፋይል ፎቶ - በቀለ ገርባ

ኦሮምያ ውስጥ በጉጂ ዞን እሥራት እየተካሄደ መሆኑ ተሰምቷል

በኦሮሞ ፌደራላዊ ኮንግረስ መሪዎች ላይ ሲካሄድ የቆየው ምርመራ ከተጠናቀቀ በኋላ እንደገና የ28 ቀናት የጊዜ ቀጠሮ መሰጠቱ አግባብ አይደለም ሲሉ የኦፌኮ የሕግ ጉዳዮች ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ወንድሙ ኢብሳ ለቪኦኤ ገልፀዋል።

የኦሮሞ ፌደራላዊ ኮንግረስ - የኦፌኮ አርማ

አቶ ወንድሙ በተጨማሪም ጥብቅና ለቆሙላዡዋ የፓርቲው አባላት የሆኑ ከ30 በላይ እሥረኞች ችሎት ፊት እንዳይቆሙ በፖሊስ መታገዳቸውን ተናግረዋል።

የኦሮሞ ፌደራላዊ ኮንግረስ መሪዎች የሆኑት አቶ በቀለ ገርባ፣ አቶ ደጀኔ ጣፋ፤ አቶ ደስታ ዲንቃ፣ አቶ ጉርሜሳ አያኖ፣ አቶ አዲሱ ቡላላ፤ አቶ ደረጀ መርጋ፣ አቶ ዓለሙ አብዲሳ አዲስ አበባ ማዕከላዊ ፖሊስ እሥር ቤት ውስጥ እንደሚገኙና ስማቸው የተጠቀሰና ሌሎችም እጅግ ብዙ ቁጥር ያላቸው ሰዎች የተያዙት በከበደና ኢሰብአዊ በሆነ ሁኔታ እንደነበረ እራሳቸው አቶ በቀለ ገርባ ለዳኛ ማመልከታቸውን ጠበቃቸው አቶ ወንድሙ ኢብሳ ተናግረዋል።

እሥሩም ታሣሪውም በጣም ብዙ እንደሆነና እሥረኞች ወደ ማዕከላዊ የሚገቡት ከመላ ኦሮምያ መሆኑን፤ እርሣቸው ብቻ እስከ 56 ለሚሆኑ ሰዎች ጥብቅና መቆማቸውን አቶ ወንድሙ ኢብሳ ገልፀዋል፡፡ በእነ አቶ በቀለ ገርባ ጉዳይ የሕግ አፈፃፀም ጥሰት መኖሩንም ጠቁመዋል።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

Your browser doesn’t support HTML5

በነአቶ በቀለ ገርባ ጉዳይ ጠበቃቸው እሮሮ አሰሙ

በማልታ የሚገኙ የኦሮሞ ብሔረሰብ አባላት በሰኔ ወር 2014 ዓ.ም ለተቃውሞ ሰልፍ በወጡበት ወቅት [ፎቶ ፋይል - ሮይተርስ]

በሌላ በኩል ደግሞ ኦሮምያ ውስጥ በጉጂ ዞን እሥራት እየተካሄደ መሆኑ ተገልጿል።

የአፋን ኦሮሞ ዝግጅት ክፍላችን ባልደረቦች ያጠናቀሩትን ዘገባ አለ ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

Your browser doesn’t support HTML5

ኦሮምያ ውስጥ በጉጂ ዞን እሥራት እየተካሄደ መሆኑ ተገልጿል