‹‹በቅርብ ዘመዶች የሚፈጸሙ ጾታዊ ጥቃቶች አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሰዋል›› የመብት ተሟጋች ትዕምርት ሽመልስ

Your browser doesn’t support HTML5

"እኔም!" በሚል የሚጠራውን የምዕራቡ ዓለም የጸረ-ጾታ ጥቃት ዘመቻ ሂደት በምሳሌነት የወሰዱ ወጣቶች ፣ኢትዮጵያዊያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ላይ የሚደርሱ ወሲባዊ ጥቃቶችን የሚያጋልጥ “Me too Ethiopia” የተሰኘ የበይነ መረብ መርሃ-ግብር ጀምረዋል፡፡ በጥቂት ጊዜ ውስጥ በርከት ያሉ በሴቶች እና ወንድ ሕጻናት ላይ የደረሱ ጥቃቶችን የሚያጋልጡ ታሪኮች እንደተጋሩበት ከመስራቾች መካከል አንዷ የሆነችው ትዕምርት ሽመልስ ትናገራለች። ሀብታሙ ስዩም አነጋግሯታል።