የሎስ አንጀለስና አካባቢዋ ኢትዮጵያዊያን የድጋፍ ሰልፍ

የሎስ አንጀለስና አካባቢዋ ኢትዮጵያዊያን የድጋፍ ሰልፍ

በሎስ አንጀለስና በአካባቢዋ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና “ዓለምአቀፍ ዳያስፖራ የተግባር ምክር ቤት” በጋራ ባዘጋጁት ሰልፍ ለኢትዮጵያ ሰላምና ቀጣይነት እንዲሁም ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድና ለሚመሩት መንግሥት ያላቸውን ድጋፍና አጋርነታቸውን ገልፀዋል።

ከትናንት በስተያ ቅዳሜ፤ መስከረም 30/2020 ዓ.ም. በተካሄደው ስላማዊ ስልፍ ላይ የተገኙት ኢትዮጵያዊያን ትውልድ ኢትዮጵያ አሜሪካዊያን “ከመስከረም ሰላሣ በኋላ በኢትዮጵያ መንግሥት አይኖርም” የሚሉ ወገኖችን እንደሚቃወሙ በሥነ ሥርዓቱ ላይ ባደረጓቸው ንግግሮችና ለአሜሪካ ድምፅ በሰጧቸው ቃሎቻቸው አሳውቀዋል። ከመንግሥቱ ጎን እንደሚቆሙም ተናግረዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

Your browser doesn’t support HTML5

የሎስ አንጀለስና አካባቢዋ ኢትዮጵያዊያን የድጋፍ ሰልፍ