በሰሜን ወሎ ዞን ቆቦ ከተማ ከማክሰኞ ጀምሮ በተቀሰቀሰ ተቃውሞና ግጭት የሰው ሕይወት መጥፋቱን ንብረት መውደሙ የሚታወስ ሲሆን በዛሬው ዕለት ወጣቶች ከየቤታቸው እየታሰሩ መሆኑን ነዋሪዎች ገልፀዋል። የክልሉ ፕሬዝዳንት ችግሩ የፓርቲው ነው ብለዋል። በስደት ላይ የሚገኘው ሲኖዶስ የወልዲያን ግድያ አውግዟል።
ዋሽንግተን ዲሲ —
Your browser doesn’t support HTML5
በቆቦ ከተማ የዛሬ ውሎ ወጣቶች እየታሰሩ መሆኑን ነዋሪዎች ገለፁ
ዛሬ ከተማዋ በከፊል የተረጋጋች ብትመስልም ቁጥራቸው የበዛ የመንግስሥት ታጣቂዎች በከተማው ውስጥ እንደሚገኙ ነዋሪዎች ተናግረዋል። የአማራ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው በአማራ ክልል ቴሌዥን ጣቢያ በሰጡት መግለጫ፤ የችግሩ መሰረት በሕብረተሰቡ ዘንድ ሲጠራቀም የቆየ ቅሬታና ብሶት መሆኑን ገልፀው ሕዝቡ የሚያነሳቸው ችግሮች የፓርቲው “ብአዴን” ችግር መሆኑን ጠቅሰዋል።
ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።