“የጥናቱ ዓላማ በውጭ አገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በትውልድ አገራቸው በሚያኪያሂዷቸው የየግል ፕሮዤዎቻቸው መተባበር የሚቻልባቸውን ዕድሎች ማየት ነው።” Gillian Williams የዓለም አቀፉ የስደተኞች ጉዳይ ድርጅት IOM አማካሪ እና የጥናቱ አስተባባሪ።
ዋሺንግተን ዲሲ —
በትውልድ አገሮቻቸው ሊያካሂዱ የሚፈልጉዋቸውን የልማት ሥራዎች፤ ዕቅድ እና ግባቸውን አስመልክቶ፤ ይልቁንም “ይበጃል” ስለሚሏቸው ምርጫዎቻቸው ምንነት ድምጻቸውን ለማሰባሰብ የታለመ ጥናት መያዙን አንድ ዓለም አቀፍ ድርጅት አስታወቀ።
በሦሥት የዩናይትድ ስቴትስ ግዛቶች የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ-ኢትዮጵያ አሜሪካውያንን ያሳተፈ ጥናት እያደረገ መሆኑን ይፋ ያደረገው ዓለም አቀፉ የስደተኞች ጉዳይ ድርጅት IOM - የጥናቱ ውጤት ተጠናቆ በባለሞያዎች እንደሚገመገም እና የትብብር አማራጮችን ለመቀየስ እንደሚውል አመልክቷል።
ከጥናቱ አስተባባሪ Gillian Williams ጋር የተካሄደውን ቃለ ምልልስ ተንተርሶ የተቀናበረ ዘገባ ከዚህ ያድምጡ።
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
Your browser doesn’t support HTML5
አይ ኦ ኤም ዋሽንግተን ዲሲ እና አካባቢው ያሉ ኢትዮጵያውያንን የልማት ፍላጎት ሊያጠና ነው