በሐይቅና ዳርቻዎቹ ላይ በሐዋሳ ከተማ የተከበረው የጥምቀት ከተራ በዓል  

Your browser doesn’t support HTML5

በሐይቅና ዳርቻዎቹ ላይ በሐዋሳ ከተማ የተከበረው የጥምቀት ከተራ በዓል  

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ዐበይት በዓላት አንዱ የሆነው የጥምቀት ከተራ በዓል በሐዋሳ ከተማ በሐይቅና ዳርቻዎቹ ተከብሯል። ጥምቀት እና ከተራ፣ በሐይቅ ዳርቻ በሚገኘው ደብረ ምጥማቅ መድኃኔዓለም ገዳም አንዱ ሲኾን በከተማው የሚገኙት ዐሥራ አንድ ደብር ታቦታት ሄደው ያደሩት በዚኽ ስፍራ ነው።

በተጨማሪም ከሐዋሳ ሐይቅ ማዶ ከሚገኘው ሎቄ ደብረ መድኃኒት መስቀለ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያ ሁለት ታቦታት በ25 ጀልባዎች ታጅበው በሐይቁ ላይ ዘጠኝ ኪሎ ሜትር ተጉዘው አንድ ላይ ያከብራሉ።

ቁጥራቸው የበዛ የእምነቱ ተከታዮች በታደሙበት የቤተ ክርስቲያን ካህናት መዘምራንና የእምነቱ ተከታዮች በሐይቁ ላይ ታቦታቱን በሕብረ ዝማሬ፣ በወረብ፣ በውዳሴ በጸሎት እና በምስጋና አጅበው በደማቅ ሥነ ሥርዐት ወደ መድኃኔዓለም ጥምቀተ ባሕር ገዳም አቅንተዋል።