በዛሬው ዕለት በጎንደር ከተማ በተቀሰቀ ግጭት የሰው ሕይወት ጠፋ። የአሜሪካ ድምፅ ያነጋገራቸው ነዋሪዎች እስካሁን የአራት ሰው ሕይወት ጠፍቷል ሲሉ የክልሉ መንግሥት እስካሁን ባለን መረጃ የጠፋው የአንድ ሰው ሕይወት ነው ብሏል።
ዋሽንግተን —
የክልሉ መንግሥት አክሎም ከግጭቱ በኋላ ንብረት መውደሙንና መዘረፉን አስታውቋል። ነዋሪዎቹ ለግጭቱ መቀስቀስ ዋናም ምክንያት በሰላማዊ መንገድ ቁጭ ብሎ የኮ/ል ደመቀ ዘውዴን ለፍርድ መቅረብ ሲጠባበቅ የነበረው ሕዝብ ላይ አስለቃሽ ጭስ መወርወሩ ነው ብለዋል።
በቦታው ነበርን ያሉ የአካባቢውን ነዋሪዎችና የክልሉን መንግሥት በማነጋገር የተጠናከረ ዘገባ ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።
Your browser doesn’t support HTML5
በጎንደር ከተማ በተቀሰቀ ግጭት የሰው ሕይወት ጠፋ