ከዋሽንግተን ዲሲና ከአካባቢው እንዲሁም ከተለያዩ የአሜሪካ ግዛቶች የመጡ ኢትዮጵያውንና ኢትዮጵያውያን አሜሪካውያን በዛሬው እለት በዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት፣ በዋይት ሃውስ እና በዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት ደጃፎች የተቃውሞ ሰልፍ አካሄዱ።
ዋሽንግተን —
Your browser doesn’t support HTML5
ግዙፍ ሰላማዊ ሰልፍ በዋሽንግተን ዲሲ
ሕጻናት የያዙ እናቶችና አዛውንቶች ጭምር የነበሩበት እጅግ የበዛ ቁጥር ያለው ሰላማዊ ሰልፈኛ ከማለዳው አንስቶ ነው “በዚያች አገር እየተካሄደ ነው” ያለውን ግድያ “በአፋጣኝ አስቁሙ!” እና “ለመንግስቱ የምትሰጡትንም እርዳታ አቋረጡ” የሚሉ ጥያቄዎችን ላቀረበላቸው የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ባለሥልጣናትና የምክር ቤት አባላት ሲያሰማ የዋለው።
Your browser doesn’t support HTML5
ቁጥሩ እጅግ የበዛ ኢትዮጵያውያን ሰላማዊ ሰልፈኛ በዋሽንግተን የተቃውሞ ድምጹን ሲያሰማ ዋለ
ሳያቋርጥ ቀኑን በዘለቀው ካፊያ ውስጥ ከውጭ ጉዳይ ሚንስቴር መሥሪያ ቤት ወደ በዋይት ሃውስ አልፎ ከምክር ቤት የሚያደርሱትን የከተማይቱን ጎዳናዎች ሞልቶ ሲሰማ የዋለውን ሰልፈኛ ድምጾች ያካተተውን ዘገባ ዝርዝር ከዚህ ይከታተሉ።
Your browser doesn’t support HTML5
ግዙፍ ሰላማዊ ሰልፍ በዋሽንግተን ዲሲ