የጎብኚዎች ቁጥር መቀነስ የጀመረው በኢትዮጵያ የተቃውሞ እንቅስቃሴ ከተጀመረ ጀምሮ መሆኑን የተናገሩት የአንዱ አስጎብኚ ድርጅቶቹ ኃላፊ አሁን ደግሞ በአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ ላይ ወዳለች ሀገር ቱሪስቶች ሊመጡ አይችሉም ብለዋል።
ዋሽንግተን ዲሲ —
በተለያዩ አካባቢዎች የተነሱት ሕዝባዊ ተቃውሞዎች፣ የተፈጸሙ ግድያዎችና ባሳለፍነው ወር የወጣው የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ መድረሻቸውን ኢትዮጵያ ያደረጉ ጎብኚዎችን ማራቁን አንዳንድ የአስጎብኚ ድርጅቶቹ ባለቤቶች ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል።
ከአስጎብኚ ድርጅቶቹ ኃላፊዎች አንዱ በአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ ላይ ወዳለች ሀገር ቱሪስቶች ሊመጡ አይችሉም ብለዋል።
ጽዮን ግርማ ዝርዝር አላት።
ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ።
Your browser doesn’t support HTML5
አስቸኳይ ጊዜ ዐዋጁ ዓለም አቀፍ ጎብኚዎችን አርቋል