ከምስራቅ ሀረርጌ የተለያዩ ቦታዎች ተይዘው ታስረው የነበሩ አንድ የ45 ዓመት ጎልማሳና አንድ የዩኒቨርስቱ ተማሪ ስለ "ጦላይ የእስረኞች ማቆያ ማዕከል" ቆይታቸው አጫውተውናል። ክፍል አንድ በትናንትናው ምሽት ቀርቦ ነበር ክፍል ሁለት በዛሬው ምሽት ይቀርባል።
ዋሽንግተን ዲሲ —
በኢትዮጵያ የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ ከታወጀ በኋላ የታሰሩ ከ11 ሺህ በላይ እስረኞች በተለያዩ ቦታዎች በሁለተኛ ዙር "የተሃድሶ ስልጠና" ወስደው መለቀቃቸው ተገልጿል። ከእነዚህ ውስጥ የበዛውን ቁጥር የሚይዙት በጦላይ የማቆያ ማእከል ስልጠና የወሰዱት እንደሆኑም የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጁ ኮማንድ ሴክረትሪያት በጥር ወር መጨረሻ ለሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ማስታወቁ ይታወሳል።
ጽዮን ግርማ ከዚህ ከጦላይ ማቆያ ማዕከል የተለቀቁ ሁለት እስረኞችን አነጋግራ ያጠናቀረችውን ዘገባ የመጀመሪያ ክፍል በትናንተናው ምሽት ማስደመጣችን ይታወሳል ሁለተኛውንና የመጨረሻውን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ።
Your browser doesn’t support HTML5
ከጦላይ የተለቀቁ ሁለት እስረኞች ስለቆይታቸው ይናገራሉ (ክፍል ሁለት)