“የአገር ጉዳይ” .. እና ሌሎች ታሪኮችየሳምንቱ የራዲዮ መፅሔት ወጎች፥

Amharic Radio Magazine Program Banner 2

የሳምንቱ የእረፍት ጊዜ የእሁድ ምሽት የቁም ነገርና መዝናኛ ምርጫችሁ ከአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ።

እስኪመለስ የቀጠለ ይመስላል፤ ሁነኛ መልስ ፍለጋው። የአገር ጉዳይ ዛሬም ያነጋግራል።

እናም ስለሚያሳስቡን ጉዳዮች ሰዓቱ ከረፈደ በኋላ ሳይሆን ዛሬ .. መነጋገር ለመነጋጋር ያህል ብቻም ሳይሆን ለመግባባት እና አንዳች ጠቃሚ መላ ለመሻት፤ መንገዱ ተጀምሯል።

በዛሬው የአገር ጉዳይ ሦሥት እንግዶች ከአዲስ አበባ ጋብዘናል።

“የሁላችንም በሆነች አገር ለሁላችንም የሚበጁ የሕይወት መላዎች” የሚሉ ይመስላል፤ የዛሬዎቹ “የአገር ጉዳይ” ባለተራዎች በወጋቸው።

የአዲስ አበባው የመጽሔት የወግ መስኮት ሲከፈት “ስለ ነፋስ” የተቀናበረ ዝግጅት በድምጹ መስኮት “ውልብ” ይላል። ከንባብ የፈጠነ ስለሚመስለው የድርሰት አጻጻፍ ፍጥነት ከአሥራ አምስት በላይ መጻሃፍት ደራሲ ጋር የተካሄደ ሌላ ወግ ተካቷል።

Your browser doesn’t support HTML5

የሳምንቱ የራዲዮ መፅሔት ወጎች “ቅምሻ”

Your browser doesn’t support HTML5

ሳምንቱ ምርጥ ግጥሞች:- “የግድግዳው ሰዓት” በዮናስ አብረሃ ፍቅርና ጃዝ በምልዕቲ ኪሮስ

Your browser doesn’t support HTML5

“የአገር ጉዳይ” .. ንግግር ከመርፈዱ በፊት -- የመጀመሪያ ክፍል

Your browser doesn’t support HTML5

የአዲስ አበባው የመጽሔት የወግ መስኮት “ስለ ነፋስ”

Your browser doesn’t support HTML5

ከንባብ ዓለም ገጾች:- ከንባብ የፈጠነ የሚመስለው የድርሰት አጻጻፍ ፍጥነት