በመንግሥት አገልግሎት አሰጣጥ ችግር ቡና በወቅቱ ለማዕከላዊ ገበያ አለመቅረቡ ተገለጸ

Your browser doesn’t support HTML5

በመንግሥት አገልግሎት አሰጣጥ ችግር ቡና በወቅቱ ለማዕከላዊ ገበያ አለመቅረቡ ተገለጸ

በሐዋሳ ምርት ጥራት ምርመራ እና ማረጋገጫ ማዕከል ገጠመን በሚሉት እንግልት እና አገልግሎት አሰጣጥ ችግር ቡናቸውን ለማዕከላዊ ገበያ በወቅቱ ማቅረብ እንዳልቻሉ የቡና አቅራቢዎች ተወካዮችና እና አሽከርካሪዎች ለአሜሪካ ድምፅ ገለጹ።

የኢትዮጵያ ቡና እና ሻይ ባለሥልጠን የምርት ጥራት መርመራ እና ማረጋገጫ ማዕከል ችግሩ የተፈጠረው በቦታ ጥበት እና ወደ ማዕከሉ የሚመጣው የምርት መጠንና የማዕከሉ የማስተናገድ አቅም ባለመጣጣሙ ነው ብሏል።

የሲዳማ ክልል ግብርና ቢሮ በበኩሉ ችግሩ መኖሩን አምኖ ለማዕከሉ አገልግሎት የሚውል የተሻለ ቦታ ለመስጠት ጥናት እያደረገ መኾኑን ገልጿል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።