በኢትዮጵያ 108 የሀገር ውስጥና 14 የውጭ ግብረ ሰናይ ድርጅቶች እንዲዘጉ ተደርጓል

ሌሎች 167 ድርጅቶች ደግሞ የጽሑፍ ማስጠንቀቂያ እንደተሰጣቸውና መሻሻል እንዲያደርጉ ዛሬ በተጠራ የምክክር ስብሰባ ላይ መታዘዛቸው ተዘግቧል፡፡

አብዛኞቹ የተዘጉት በጀት አጥተው እንደሆነ የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማኅበራት ኤጀንሲ የኮሙዩኒኬሽን የሥራ ሂደት ባለቤት አቶ አሰፋ ተስፋዬ ለቪኦኤ ገልፀዋል።

የህግ ባለሞያና ለረጅም ጊዜ የበጎ አድራጎት ድርጅቶችን በማማከር የሚሠሩት አቶ ደበበ ኃይለገብርዔል “ለድርጅቶቹ መዘጋትና መዳከም ምክንያቱ ሕጉና ሕጉን የሚያስፈፅሙት የኤጀንሲ ሠራትኞች” ናቸው ይላሉ።

ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።

Your browser doesn’t support HTML5

በኢትዮጵያ 108 የሀገር ውስጥና 14 የውጭ ግብረ ሰናይ ድርጅቶች እንዲዘጉ ተደርጓል