“የምንሠራውን ነገር በሙሉ በግልጽና በተጠያቂነት ነው የምናደርገው ብለናል። ገንዘብ እንዴት እንደምንሰበስብ፣ ማን እንደሰጠ ማን እንዳልሰጠ ሁሉ ነገር ግልጽ ነው። እኛ ብቻ የምናወራውን ሳይሆን .. የተሰበሰበውን መረጃ ተመልክቶ ከየት እንደመጣ .. ራሱ አይቶ እንዲገነዘብ ነው።” ፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማሪያም የኢትዮጵያውያን ተራድዖ ባለ አደራ የአማካሪ ቦርዱን ሊቀ መንበር።
ዋሽንግተን ዲሲ —
Ethiopian Diaspora Trust Fund በሚለው የእንግሊዝኛ መጠሪያው የሚታወቀው በውጭ አገሮች ነዋሪ ከሆኑ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ-ኢትዮጵያውያን ለኢትዮጵያ ልማት መርጃ የሚውል ገንዘብ የሚያሰባስበው ባለ አደራ ቦርድ እስካሁን ያሰባሰበው ገንዘብ ከአንድ ሚልዮን ዶላር መብለጡን ይፋ አደረገ።
“አንድ ዶላር በቀን” ሲሉ ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አሕመድ ያቀረቡትን ጥሪ ተከትሎ የተዋቀረው ቡድን ለውጥኑ መሳካት ያለውን ተሥፋና “አሉ” ያላቸውንም ፈተናዎች ጠቁሟል። ይህንኑ ዜና መሠረት በማድረግ በአዲሱ ዓመት ዋዜማ የአማካሪ ቦርዱን ሊቀ መንበር ፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማሪያምን አነጋግረናል።
(ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ)
Your browser doesn’t support HTML5
የኢትዮጵያውያን ተራድዖ አሰባሳቢ ባለ አደራ ቦርድ የሚልዮኑን ዶላር እርከን አለፈ