የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ዛሬ ጥር 16 ቀን 2017 ዓ.ም በአወጣው የሩብ ዓመት ሪፖርት፣ በኢትዮጵያ በግጭት ዐውድ ውስጥ በሚገኙ አካባቢዎች በአለፉት ሦስት ወራት ውስጥ በተካሄደ የምርመራ ሪፖርት ከ200 በላይ ሲቪሎች ከፍርድ ውጭ መገደላቸውን አስታወቀ።
Your browser doesn’t support HTML5
በኢትዮጵያ በሦስት ወራት ውስጥ ከ200 በላይ ሲቪሎች ከፍርድ ውጪ መገደላቸውን ኢሰመኮ አስታወቀ
ግድያዎቹ የተፈፀሙት በመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች እና በየክልሎቹ በሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች እንደሆነም ኮሚሽኑ አመልክቷል፡፡
በሲቪሎች ላይ ከፍርድ ውጭ የሚፈጸሙ ግድያዎች አሳሳቢ ሆነው መቀጠላቸውን የገለጹት የኮሚሽኑ ተጠባባቂ ዋና ኮሚሽነር ራኬብ መሰለ፣ ለዚህ ምክንያት የሆኑ ግጭቶች እንዲቆሙ እና በተለይም መንግሥት ኃላፊነቱን እንዲወጣ ጠይቀዋል። የኢትዮጵያ መንግሥት እስከ አኹን በጉዳዩ ላይ ምላሽ አልሰጠም።