በሰሜን አሜሪካ የሚኖሩ የትግራይ ካህናት ማኅበር አባላት ሰልፍ አካሄዱ

Your browser doesn’t support HTML5

በሰሜን አሜሪካ የሚኖሩ የትግራይ ካህናት ማኅበር አባላት ሰልፍ አካሄዱ

በኢትዮጵያ ትግራይ ክልል “ቀጥሏል” ያሉት ግፍና በደል እንዲቆም፣ እርዳታ እንዲደርስና ሁሉም ወገኖች ለተፈጠሩት ችግሮች ወደ ሰላማዊ መፍትኄ እንዲዞሩ በሰሜን አሜሪካ የትግራይ ካህናት ማኅበር አባላት ጠየቁ።

ካህናቱ ድምፃቸውን ያሰሙት ዋሽንግተን ዲሲ ውስጥ በውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤቱ ደጅ ላይ ትናንት በአካሄዱት ሰልፍ ነው።

ሰልፈኞቹ ጥያቄዎቻቸውን ለውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤቱ ባለሥልጣናት ማቅረባቸውም ተናግረዋል።