ዶናልድ ትራምፕ ማናቸው?

Your browser doesn’t support HTML5

አንዳንዶች ትራምፕ በሰባት አመታቸው የነበራቸውን ባህሪ በ70 ዓመታቸውም አልቀየሩም ይሏቸዋል ቢሊየነሩን የንግድ ሰው ዶናልድ ጆን ትራምፕን ሪፐብሊካን ፓርቲ ለአሜሪካ ፕሬዝዳንትነት በይፋ እጩ አድርጎ መርጧቸዋል።ለመጪው ፕሬዝዳንታዊ ውድድርም ከቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ቢል ክሊንተን ባለቤት፣ ከቀድሞ የአሜሪካ ሴናተርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዲሞክራቷ እጩ ፕሬዝዳንት ሂላሪ ክሊንተን ጋር መፋጠጥ ይጠብቃቸዋል። ምንም ፖለቲካዊ ልምድ የሌላቸው ነጋዴው ትራምፕ የአሜሪካ እጩ ፕሬዝዳንት መሆናቸው ቁርጥ ሆኗል። ይህ ደግሞ ለዘመናዊው የአሜሪካ ፖለቲካ ያልተለመደ ነው።